text
stringlengths
0
11.4k
የመጽሐፉን ሐሳብ አስቀድመው ላንዳንድ ሊቃውንት ሲገልጹላቸው በምስጢሩ የተደሰቱ ቢሆንም÷ ሊመጣ የሚችለውን መከራ ሲፈሩ ስላዩ ግን እኔው ብቻዬን እወጣዋለሁ ብለው÷ መጽሐፉ ገና ከማተሚያ ቤት ሳይወጣ ከፓትርያርኩ ጀመረው ለጳጳሳቱ አንድ÷ አንድ ኮፒ ላኩላቸው፡፡ ይህን ያደረጉትም አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉባኤ (በቅዱስ ሲኖዶስ) እንዲጠና በማሰብ ነበር፡፡ ሆኖም ሐሳባቸውን በሚገባ የተገነዘበላቸው ባለ መኖሩ ስደት ተነሣባቸው፡፡
በመጀመሪያ የይግባኝ መብት ተነፍገው በፓትርያርኩ ግቢ ውስጥ ጠባብና ቈሻሻ በሆነች ክፍል ውስጥ ለ5 ቀናት ያህል ከሰው እንዳይገናኙ ተደርገው ታስረዋል፡፡ ከዚያ ወደ አርሲ ተግዘው በአሰላ ከተማ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሰው ሳይገናኙ እስረኛ ሆነዋል፡፡ በእስር ላይ እያሉም በጠና ስለ ታመሙ ወደ ናዝሬት ሄደው ሕክምና እንዲከታተሉ ከተደረገ በኋላ÷ የግዞቱ ቦታ እንዲለወጥላቸው በሐኪም ተወስኖ ወደ ጅማ ተልከዋል፡፡
በጅማ ሳሉ ከንጉሡ ጋር ተጻጽፈው አንዳንድ መሻሻሎች የተደረጉላቸው ሲሆን÷ ከቤተ ክህነት በደብዳቤ ጥሪ ተደርጎላቸው ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ ሲመጡ ነገሮች ተሻሽለው የሚጠብቋቸው መስሏቸው ነበር፡፡ የሆነው ግን በመጀመሪያ በታሰሩባት ቈሻሻ ክፍል ውስጥ ዳግም መታሰር ነበር፡፡ ለግዞትና ለእስር ምክንያት የሆነውን መጽሐፍ የጻፉት በስሕተት መሆኑን አምነው ይቅርታ መጠየቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ቤተ ክህነቱ አዘጋጅቶ እንዲፈርሙበት ከአንዴም ሦስት ጊዜ ጠየቃቸው፡፡ ብፁዕነታቸውም ለመፈረም ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዳኝነት እንዲታይላቸው ንጉሡን ቢያስጠይቁ ጃንሆይ “እኛ በዚህ ነገር ዳኝነት ለማየት አንችልም፤ በዚሁ ወረቀት ይፈርሙና አርፈው ይቀመጡ” የሚል መልእክት በልዑል ራስ እምሩና በሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅ ነህ በኩል ስለላኩባቸው÷ ፍትሕ በሌለበት ሁኔታ መፍጨርጨሩ ዋጋ እንደሌለው በመገንዘብ÷ እጃቸው ባልጻፈውና ልባቸው ባላመነበት ወረቀት ላይ ተገደው ፈረሙ፡፡ ልዑል ራስ እምሩም ከጳጳሳቱ ጋር አስታረቋቸው፡፡ ይሁን እንጂ ዕርቁ ሥርዐታዊ እንጂ ልባዊ ስላልነበረ÷ በውጭ አባታችን እየተባሉ ግፉን ተሸክመው እንደ ኖሩና ከቁም እስር እንዳልተላቀቁ ገልጸዋል፡፡
ተደረገ የተባለውን ዕርቅ ተከትሎ ታኅሣሥ 22/1958 ዓ.ም በወጣው በዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ 21ኛ ዓመት ቊጥር 4 ላይ እና በዐዲስ ዘመን ጋዜጣ 25ኛ ዓመት ቊጥር 452 ግንቦት 19/1958 ዓ.ም. የወጡት መረጃዎች÷ ብፁዕ አቡ ፊልጶስ ባወጡት መጽሐፍ መሳሳታቸውን እንዳመኑና ይታረም ዘንድ እንደ ተስማሙ የሚያመለክቱ ነበሩ፡፡ ብፁዕነታቸው ግን በቤተ በክህነቱ በተዘጋጀው ወረቀት ላይ ተገደው ከመፈረም በቀር÷ በዚያ ጊዜ “በመሳፍንት ትንፋሽ በሚመራው” ባሉት ሲኖዶስ ፊት ቀርበውና ተጠይቀው የሰጡት አንዳች መልስ እንደሌለ ያረጋግጣሉ፡፡
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን ለዚህ ሁሉ መከራ ያደረሷቸው ንጉሡ መሆናቸውን የተረዱት በኋላ ላይ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በኢየሩሳሌም ሳሉ በጻፉላቸው አንዳንድ ደብዳቤዎች አለ መደሰታቸው ሳይሆን አልቀረም፡፡ በርግጥ የብፁዕነታቸው ማሳሰቢያዎች ደፋሮች ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ሁሉን ሊጠቅም የሚችል ሕገ መንግሥት በዕውቅ የሕግ ሊቃውንት እንዲዘጋጅ ያድርጉ ሲሉ÷ በ1923 ዓ.ም. እና በ1948 ዓ.ም. ንጉሡ ያወጧቸው ሕገጋተ መንግሥት ጕድለቶች እንዳሉባቸው የሚጠቊም ነው፡፡ ንጉሡ በዚህ ቢከፉና ብፁዕነታቸውን በተገለጸው መንገድ እንዲቀጡ ቢያደርጉ ብዙም የሚደንቅ አይደለም፡፡ ማሳሰቢያዎቹ በንጉሡ ዘንድ ተሰሚነትን ቢያገኙ ኖሮ ግን የንጉሡ ፍጻሜ እንዲያ ባልከፋ÷ ኢትዮጵያንም ወደ ተሻለ ሁኔታ ባደረሷት ነበር፡፡ ነገር ግን “ካቀዱት ሳይደርሱ ጊዜ እንዳይቀድምዎ ... ጊዜውን ይቅደሙት” ለሚለው የብፁዕነታቸው ምክር ጆሮ ዳባ ስላሉ እንደ ተባለው ጊዜ ቀደማቸው፡፡
“ይትፌሣሕ ጻድቅ ሶበ ይሬኢ በቀለ - ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል” ተብሎ እንደ ተጻፈ (መዝ. 57(58)÷10)÷ ብፁዕነታቸው በመጨረሻ ላይ መከራ ያደረሱባቸውን÷ “ልብንና ኵላሊትን የሚመረምረው አምላክ በአናጋሪው መንግሥት በተናጋሪው ካህን ላይም የፈጸመውን አምላካዊ ፍርድ በመሬት ላይ ቆሜ እየተመለከትሁ ኰናኒ በጽድቅ ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ሲሉ ጽፈዋል፡፡
ሆኖም በመጀመሪያው ገጽ ላይ “መልእክት የክርስቶስን አዳኝነት ለተቀበለ ክርስቲያን ሰው ሁሉ” በማለት የሚጀምረውንና “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” የተሰኘውን ሁለተኛ መጽሐፍ የጻፉበት ዋና ምክንያት “ያለፉትን ሰዎች ለመውቀሥ ሳይሆን÷ ተከታዩ ትውልድ እንዲመከርበት ነው” ይላሉ፡፡ በማስከተል “መሓሪ ይቅር ባይ እግዚአብሔር ያለፉትን ይቅር ይበላቸው፤ ተከታዮችንም ይህን የመሰለ ስውር ኀጢአት ከመሥራት ያድናቸው ስል ቅዱስ ይቅርታውን እለምናለሁ” በማለት መጸለያቸውም ለጠላቶቻቸው ያሳዩትን የፍቅር ልብ ሊያሳይ ይችላል፡፡
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ኅዳር 11 ቀን 1974 ዓ.ም. በተወለዱ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በብዙ መከራ ወዳገለገሉት ጌታ በክብር ሄደዋል፡፡ ሥርዐተ ቀብራቸውም በኢየሩሳሌም ተፈጽሟል፡፡
ራሱን ያለ ምስክር ያልተወው ቅዱስ እግዚአብሔር÷ በዘመናት ሁሉ ለመንግሥቱ ሥራ የሚቀኑና ስለ ስሙ መሥዋዕትነትን ለመክፈል በነፍሳቸው የሚወራረዱ አገልጋዮች አሉት፡፡ እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ግን ብርቅ ናቸው፤ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ብልጭ ብለው ድርግም የሚሉ፡፡ ታሪካቸውና የሥራቸው ፍሬ ግን መካን አይደለም፡፡ ሠላሳ፣ ስድሳና መቶ ዕጥፍ የሚያፈራና ዘመን ተሻጋሪ ነው፡፡ የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ተጋድሎና የአገልግሎት ፍሬ÷ አሁን ላለው ክርስቲያን ትውልድ÷ ወንጌል በነፍሱ የሚወራረድ ቈራጥ ክርስቲያንን እንደሚፈልግና ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍልም ያስተምራል፡፡
ቤተ ክርስቲያን አንዲትና የማትከፈል በመጽሐፍ ቅዱስም የምትመራ የክርስቶስ አካል መሆኗ ቢታወቅም በምድር ላይ ተከፋፍላ ትታያለች፡፡ ይህ የጠላት ሐሳብ እንጂ የእግዚአብሔር ሐሳብ ስላልሆነ÷ አሁን ያለችው ቤተ ክርስቲያን ልዩነትን ከማስፋት ይልቅ ልዩነትን በማጥበብና ከራስ ባህል ይልቅ ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ በመስጠት÷ ብፁዕነታቸው እንዳሉት÷ “በእምነትና በጥምቀት ከሚመስሉን ከክርስቲያኖች ወንድሞቻችን ጋራ የፍጡር አእምሮ ሊደርስበት በማይቻል በመለኮታዊ ባሕርይ ምርምር መጣላት አይገባም፡፡” ከዚህ ይልቅ በክርስቶስ ትእዛዝ በፍቅር ሆኖ ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት በጋራና በመረዳዳት መሥራት ክርስቲያንነት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን ከራሷ ልጆች በየዘመናቱ የሚቀርብላትን የለውጥ ጥሪ ሳትፈትሽና ሳትመረምር ቀድማ ከምትገፋው ይልቅ÷ በልበ ሰፊነት ተቀብላ ብትመረምረውና የተሻለና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይቃረን ሆኖ ካገኘችው ብትጠቀምበት መልካም ነው፡፡ ብፁዕነታቸው ያቀረቧቸውና ያስተላለፏቸው የለውጥ ጥሪዎች ብዙዎቹ ተፈጻሚ እየሆኑና ተቀባይ እያገኙ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ለጥሪው ምላሽ ያልሰጡትም ለጊዜው ቢመስልም ለውጡን አፍነው መያዝ ግን አልቻሉም፡፡ ዛሬም ለውጥን በደፈናው ከመቃወም ይልቅ ተቀብሎና መርምሮ ተገቢውን ምላሽ መስጠት አስተዋይነት ነው፡፡
ሰውየው የክርስትና ሃይማኖት በሚገባ የገባቸውና ቃሉ የሚናገረውን ትምህርቱንም ለመኖር የተጉ ሰው ነበሩ፡፡ ከቤተ ዘመድ ጠይቄ እንደተረዳኹት ከቤተ ክህነቱ (ከቤተ ትክነቱ/ ከቤተ ምክነቱ) እስር ከወጡ በኋላ እስከ ዕድሜያቸው ፍጻሜ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር አላት የሚባለው ብቸኛው ነገረ ክርስቶስን የተመለከተ ልዩነት እንደሌለ አስረግጠው ይናገሩ ነበር፡፡ ጉባኤ ኬልቄዶን ላይ የቀድሞው የነቅዱስ ቄርሎስ ሃይማኖት ተብራራ እንጂ አዲስ የተረቀቀ ሃይማኖት እንደሌለ አሳምረው ዐውቀውት ነበረ፡፡ ጉባኤው በተካኼደበት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን በነበሩ ጳጳሳት መካከል የነበረውን ፍጹም ኢክርስቲያናዊ የኾነ ፖለቲካዊ ሽኩቻና ሽኩቻው የወለደው ሃይማኖትን መጠቀሚያ ያደረገ “እነእገሌ መናፍቃን ናቸው፡፡” የሚል የሐሰት ፕሮፓጋንዳ አንዳች የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖር ቤተ ክርስቲያንን እንዴት እንደለያያት መገንዘብ ችለው ነበር፡፡
ልክ ዛሬ አሜሪካን ያለውና ኢትዮጵያ ያሉት “ሲኖዶሶች” አንዱ ሌላውን “መናፍቃን ናቸው፤ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አፍራሾች ናቸው!” እያለ እንደሚወጋገዙት መኾኑ ነው፡፡ ኹለቱም በሚያወጧቸው መግለጫዎች ራሳቸውን የሃይማኖቱ ጠበቃ አድርገው ሲያቀርቡ እንጂ እኛ ሥልጣናችን እንዳትነካብን፣ ምቾታችን እንዳትጎድልብን ነው ብለው ተናግረው አያውቁም፡፡ እነርሱ ሲሞቱ የሚቀጥለው ትውልድ ይኽን ፖለቲከኛነታቸውንና የሥልጣን ጥማቸውን ስለማያውቅ መግለጫ እያሉ በሚለቀልቋቸውና በሚለፍፏቸው ጽሑፎች ላይ ተመርኩዞ እውነት የሃይማኖት ልዩነት ያለ ይመስለው ይኾናል፡፡ ብፁዕነታቸው አቡነ ፊልጶስ ግብፆች እነርሱ ከዓለም የክርስቲያን ወገኖች ተገንጥለው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንም ገና በአፍላነት ዕድሜዋ እንደገነጠሏት ይኽም የኢትዮጵያን ክርስትና በጊዜ ኺደት ብስል ከጥሬ የተቀላቀለበት፣ ክርስትና በሚል ስም ክርስቲያናዊ ያልኾኑ ነገሮች የተሠገሠጉበት፣ ክህነትና ጥንቆላ አንድ ላይ ተዳብለው የሚኖሩበት እንዲኾን እንዳደረገው ያስተዋሉ ይመስለኛል፡፡ ለነገሩ እነርሱ በ1973 እ.አ.አ. ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር በነገረ ክርስቶስ ልዩነት እንደሌላቸው በጋራ ባወጡት መግለጫ ሲገልጹ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን “የት ነበርሽ?” ብለው እንኳ ያማከሯት አይመስለኝም፡፡ እነርሱ ዘመኑን አስተውለው የአባቶቻቸውን ስሕተት መርምረው ለመሻሻል ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ እውነቱን የሚያውቁ የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ሊቃውንት ግን ዛሬም በፍርኀት ተሸማቅቀው ይኖራሉ፡፡ አቡነ ጳውሎስ እንኳ የሚያውቁትን እውነት መናገር ፈርተው ነበር የኖሩት፡፡ እውነቱ ግን ይኸው ነው፡፡ እስኪ ደግሞ ስለ ሊቁ ዓለማየኹ ሞገስ አስነብቡንና “ኹሉም ኹሉን ይወቅ፡፡”
የድረ ገጽ መረብ (ወይም ኢንተርኔት) በጣም ብዙ የኮምፒዩተር አውታሮችን ያያየዘ የመገናኛ መረብ ነው። በመረቡ ውስጥ ብዙ ድረ ገጽ ይገኛሉ። ከዚያ በላይ በርካታ የመነጋገርና መገናኘት መንገዶች አሉ።
ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ክፍለ-ኢንተርኔት «USENET» የሚባለው አገልግሎት ነው። ይህ በ1973 ዓ.ም. (1980 እ.ኤ.አ.) አካባቢ ሲጀመር በተለይ ለዩኒቨርሲቴዎችና ኮሌጆች ብቻ የታወቀ መገናኛ ሆኖ ቆየ። ይህ ጽሑፍ በተገናኙት ኮምፒውተሮች ላይ መልጠፍ የሚፈቅድ ሥርዓት ብቻ እንጂ ስዕል ወይም ሌላ ነገር አልነበረም። መጀመርያው e-mail አድራሳዎች የተሰጡት ከዚያ ዘመን ነው። ዛሬም ብዙዎች ተጠቃሚዎቹ ግን ስንኳ ስለ USENET መኖሩን አያውቁም።
ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሰራ ለመረዳት በመጀመሪያ አገልጋይና (server) ደንበኛ (client) ምን እንደሆኑ ለይተን እንረዳ። አንድ የምግብ ቤት አስተናጋጅ ምግብ ለብዙ ተስተናጋጆች እንደሚያቀርበው፣ ሁሉ ኢንተርኔት ላይ ያለ አገልጋይ (server) የተለያዩ ነገሮችን ደንበኞቹ (clients) ይሰጣል። የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ደንበኞች ይባላሉ ማለት ነው።
ደንበኞች የተለያየ ነገር ከአገልጋዩ ሊቀበሉ ይችላሉ። ለምሳሌ፤ እርስዎ ይህንን ድረ ገጽ ሲመለከቱ የቻሉት አገልጋዩን ድረ ገጹን እንዲልክልዎ በመጠየቅዎ ነው። በመሆኑም ይሄ አገልጋይ «ድረ ገጽ አገልጋይ» (web server) ይባላል። ሌላ አገልጋይ ደሞ መልአክት (email) ሊያቀብል ይችላል። ስለዚህም «መልአክት አገልጋይ» ይባላል።
ኢንተርኔት የአገልጋይና የደንበኞች መረብ ነው። በአብዛኛው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ድረ ገጽ (WWW or World Wide Web) ይጠቀማሉ። ስለዚህም ደረ ገጽ የኢንተርኔት ትልቁ ጥቅም ነው። ብዙ ጊዘም ኢንተርኔትና ድረ ገጽ በስህተት አንድ መስለው ይታያሉ። ነገር ግን መረቡ፤ ማለትም ኢንተርኔት፤ ለሌላ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ለምሳሌ ከላይ የተጠቀሰው (USENET) የኢንተርኔት ሌላው ጥቅም ነው።
ከአንድ አገልጋይ የሚፈልጉትን ነገር ለመጠያቅ በመጀመሪያ የአገልጋዩን መጥራት ያስፈልጋል። እያንዳንዱ አገልጋይ ልዩ የሰነድ አድራሻ (URL) አለው። ይሄን የሰነድ አድራሻ በመጠቀም ከየትኛውም ቦታ አገልጋዩን መጥራት ይቻላል። ለምሳሌ www.wikipedia.org የውክፔድያ አገልጋይ የሰነድ አድራሻ ነው። አንዳንዴ አንድ ነገር ፈልገን የትኛው የሰነድ አድራሻ ላይ አንደምናገኘው ላናውቅ እንችላለን። በዚህ ጊዘ ፈላጊዎችን (search engines) እንጠቀማለን። ለምሳሌ www.google.com ጉግል ላይ የሰነድ አድራሻዎችን መፈለግ ይችላሉ።
ንፈተና ካብ ዝቐርቡ 121,100 ተምሃሮ ሻምናይ ክፍሊ፣ 186,672 ተምሃሮ ዓስራይ ክፍሊ እንትዀኑ 16,859 ተምሃሮ ዓሰርተ ክልተ ክፍሊ ከምዝዀኑ ብምሕባር ኣብ ዘበነ ትምህርቲ 2010 ንፈተና ዝተዳለዉ ቊፅሪ ተፈተንቲ ተምሃሮ ምስ ሕሉፍ ዓመት እንትነፃፀር ኣብ ሻምናይ ክፍልን ዓስራይ ክፍልን ወሰኽ እንትህልዎ ኣብ ዓሰርተ ክልተ ክፍሊ ግን ከምዝቐነሰ ወይዘሮ ኣለም ኣዘኻኺረን ፡፡
ወይዘሮ ኣለም፣ ኣብ ዘበነ ትምህርቲ 2009 ዓ.ም ኣብ ዓስራይን ዓሰርተ ክልተን ኣብ ከይዲ ፈተና ፀገማት ከምዝነበሩን ቢሮ ትምህርቲ ክልል ትግራይ ንዝተፈፀሙ ፀገማት ብምልላይ ዝተፈላለዩ ስጕምትታት ከምዚወሰደ ዘፍለጣ እንትዀን ካብኣቶም ዝተቐዳድሑ 37 ተምሃሮ ዓስራይን ዓሰርተ ክልተ ክፍልን ፈተነኦም ምሉእ ንምሉእ ከምዝተሰዘ፤ ኣብ እዋን ፈተና ሻምናይ ክፍሊ ጥቡቕ ክትትል ዘይገበራ 36 ኣብያተ ትምህርቲ በብደረጅኡ ዝተፈላለየ ስጕምቲ ከምዝተወሰደለን፣ ኣብተን ኣብያተ ትምህርቲ ተፈቲኖም ልዑል ነጥቢ ዘምፁ ተምሃሮ ናብ ቀላሚኖ ከይወዳደሩ ዝተገበረ እንትኸውን፤ ብኣግባቡ ዘይፈተኑ መምህራን ሱፐርቫይዘራት ድማ ክሳብ ሓደ ወርሒ መሃየኦም ከምዝተቐፅዑን ኣብ ዘበነ ትምህርቲ 2010 ዓ.ም. ከይፍትኑ ከምዝተኣገዱን ሎሚ ዘበን እውን ነፍሲ ወከፍ ተምሃራይ ናይ ባዕሉ ፈተና ክሰርሕ፣ ፈተንቲ መምህራን ይኹኑ ሱፐርቫይዘራት ብኣግባቡ ክፍትኑ ግቡእ ክትትል ከምዝግበር ኣፍሊጠን፡፡
ሃገራውን ክልላውን ፈተና ዝወሃበሉ ጊዜ ዓስራይ ክፍሊ ካብ ጕንበት 22 -24፣ ዓሰርተ ክልተ ክፍሊ ካብ ጕንበት 27 -30 እንትኸውን ሻምናይ ክፍሊ ድማ ካብ ሰነ 5 -7 ከምዝዀነ ዳይሬክተር ምዘና ትምህርትን ብሄራዊ ፈተናታትን ወይዘሮ ኣለም ነጋ ኣዘኻኺረን፡፡
እንታይ መሰረት ዝገበረ ኢዩ ዝብል ሓሳብ ስለ ዝፋራረቐኒ ኢዩ፡ቃልሲ ህዝቢ ኤርትራ ካብ ዝጅምር ነቲ ኣብ ዝተፈላለየ እዋናትን መድረኻትን ዘጋጥም ዝነበረን ዝቅጽል'ውን ዘሎን መሰናኽል ፡ ኣብ ኤእዋኑ ሳኣን ምፍታሕን ፡ እቲ ክኸውን ዝግብኦ ናይ ምእላይ ኣጋባብ ሳኣን ምፍላጥን ኣብ ርእሲ ጊዜ ምውሳዱ እናታሓላለኸ ይኸይድ ስለ ዘሎ፡ኣብ መጻኢ ካብ ጌጋ ምእንቲ ክንድሕን ብግቡእ ክንሓስበሉን ጥብቃቐ ክንገብርን ይግባእ።
ብኣውርኡ ካኣ ጠቕምና ስኣን ምልላይ እዩ፡ ማለት ሓደ ህዝቢ ጥቕሙ እንተ ኣለልዩ መጋበርያን ባርያን ነናይዝመጹ ገዛእትን ስዒቦቦም ናይ ዝመጹ ሃገራውያን መሰል ተበጽትን ኮይኑ ክነብር ኣይፈቅድን ኢዩ፡ ኩልና ከም ንፈልጦ ኩሎም እቶም በብእዋኑ ኣብ ዓለም ዝተራእዩ ረገጽቲ ህዝቢ ዝኾኑ ዲክታቶራትን ተበለጽትን ካብ ናይ ርእሶም ጠቕሚ ወጻኢ ካልእ ዘይርእዩን ሱሱዓትን ኢዮም፡ ክሳፅ እታ ኣብ ስልጣን ዘለው ካኣ ካብ ክፉእ ምግባርን ንህዝቢ ምብዳልን ድሕር ዘይብሉ ፍጡራት ኢዮም፡፡
ሓልዮ ናይ ዝኾነ ይኹን ህዝቢ ይኹን ሃገር ስለ ዘይብሎም ካኣ እዚ ዝቕጥቅጠና ዘሎ ፍላይ ማንታኦም ዝኾነ ኣረሜናዊ ጉጅለ ፡ ኣብ ኤርትራ ጠቕሙ ፈሊጡ ፡ ንሕና ካኣ ግቡእናን መሰልናን ሳኣን ምፍላጥን ፡ ነቲ ኩሉ ዝገብሮ ክፋእ ሳኣን ምልላይን ፡ ኩሉ እንትናና ንኣኻ ንብሎ ኣለና፡ እዚ ድማ ሓደ ኣብ ዓለም ካብ ዘገርሙ ተርእዮታት ኢዩ ምኽንያቱ ሓደ ተቓላሳይ ህዝቢ እናተባሃልካስ፡ ካብ እቲ ተቓሊስካ ዝሳዓርካዮ ንዝገድድ ኩነታት ተቐቢልካ ክትነብር ዝእመን ኣይኮነን፡ ግን ጎዳእትኻ ንዝገብርዎ ብማፅረ እንተ ዘየለሊኻዮ ንምልጋሶም ሓይል ኢዩ ፡ እዚ ኩሉ ዝካየድ ዘሎ ቃልሲ ተግባሮም ኣለሊና ንምልጋሶም ክንበቅፅ እሞ እቲ ዝደለ ሰላም ንኸነስተማቕር ኢዩ፡፡
ዝኾነ ኮይኑ፡ ኣብ'ዚ እዋን እዚ፡ እቲ ኣብ ኤርትራ ዘሎ ግናይ ስርዓት፡ ንመላእ ህዝቢ ከም ናይ መጓሰ ማሉ ንኤርትራ ካኣ ከም ሕዛእቱ ጌሩዋ ኣሎ፡ ንመሰሉ ዘለለየ ህዝቢ ግን ሓደ ንበይኑ ምስ ዝተወሰኑ ጭፍራ ኮይኑ ክጭፍጭፎ ኣይክእልን ኢዩ፡ ንሕና ሳኣን ዝኸውን ምፍላጥናን ሳኣን ስምምፅናን ባፅልና ንባፅልና ንቃጣቐጥን ንሳቐን ከም ዘለና ክርዳኣናን፡ ንምፍትሑ ክንራዳዳእን ኣለና፡ መሰልና ካብ መሰል ናይቶም ዝቕጥቅጡና ዘለው ይዓቢ ሳኣን ምፍላጥናን ሓደ ኴና ንመሰልና ጠጠው ሳኣን ምባልናን ግን ብኦም ንርገጽ ኣለና፡ ሓድነትና ኣደልዲልና ክንገብሮ ዘለና ንፍለጥ ጥራይ እየ ዝብል፡፡
ምኽንያቱ ነቲ ቀታሊና እንብሎ ዘለና ስርዓት ኢዱን እግሩ ንሕና ኢና፡ ባፅዳዊ ገዛኢ እኮ የብልናን፡ ወታሃደር ይኹን ሓኪም ይኹን ጽሓፋይ ወይ ካልእ ዝኾነ ስራሕ ዝሰርሕ ኤርትራዊ ኢዩ፡ ኩሉ ተሳማሚዑ ሓንቲ ማዓልቲ ኣብ ገዝኡ እንተውዒሉ ጸቓጢ ዝብሃል ኣካል የለን፡ ስለ'ዚ ስኣን ምርድዳእን ሓደ ምዃንን ጥራይ ኢና ኣብ ስቓይ ንነብር ዘለና፡ ሓደ ምዃን ጥራይ ጸላኢኻ ስዒርካ ነጻ ዝገብር ካብ ኮነ፡ ንምንታይ ኣሕዋት ሓደ ዘይንኸውን፡ ስለ'ዚ ሓድነት እቲ ወሳኒ ሓይሊ ካብ ኮነ ንምታይ ቃልስና ብዝልዓለ ንሓድነት ጥራይ ኣይኸውንን፡ ሕጂ ግን ናይ መወዳእታ ዳኣ ንሕስበሉ።
ይኹን እምበር እዞም ዝተወሰኑ ጭፍራ ኣብ ጽፍሒ እቲ ማእለያ ዘይብሉ መስዋእቲ ዝተኸፍሎ ሃገራዊ ናጽነት ተረቂቖም ብተንኮል ስለ ዝሓዙና ዝኾነ ይኹን ጠቕሚ ኣይረኸብናን ጥራይ ዘይኮነስ ነታ ሃገር ዋላ ከምቲ ኣብ ትሕቲ ባፅዳውያን ከላ ዝነበረቶ ምስ ሓሳረ መከራና ብሰላም ክንነብራ እውን ኣይፈቐዱልናን፡ እሞ ኣሕዋት ኣብዚ ነጥቢ እንታይ ትብሉ፡ እዚ ወሪዱና ዘሎ ንኹሉ ጊዜ ክንጽመሞ ዝካኣል ኣይኮነን፡ ምኽንያቱ ካኣ ኩሉ ኣብ ሞንጎና ሓድነት ሰሪ ዘይምህላው ጥራይ ዝወርደና ዘሎ ኢዩ፡፡
ማለት እዚ ኩነታት ከምኡ ኢሉ፡ እቲ ግዝኣት ቱርኪ እናተባህለ ዝንገረና ዝነበረ ሕሰም ናይ መግዛእቲ ኣብ ዘለዎ መልክዑ እናቐያየረ ከምቲ ዝነበሮ ወይ ዝገድድ ኮይኑ ይነብር ኣሎ፡ ስለ'ዚ ነዚ ነባሪ ኮይኑ ዝጸንሐን ጌና'ውን ዝቕጽል ዘሎን ሃገራዊ ጸገምን ህዝቢና ዘሕልፎ ዘሎ ካብ መጠን ንላፅሊ መሪር ዝኮነ ሽገርን፡ ኣብ ንቡር ንምምላስ ካልእ ጓል መገዲ ገዲፍና ንዘሎ ሽግርና ንምፍታሕ ዝላዓለ ጻፅሪ ከነካይድ ኢዩ ኣለና።
ኣብ ኣየናይ መድረኽን እንታይ ዝዓይነቶም ወለዶ ምስ መጹን ኢዩ፡ እዚ ህዝቢ እዚ ካብ መግዛእቲ ተገላጊሉ ዝቐስንን ሰላም ዝረክብን፡ ክቡራት ኣሕዋት ሓደ ብምዃን ንኹልኻ ብማፅረ ዘናብር ሕጊ ምውጻእ የድሊ ኣሎ፡ ሓንቲ ሃገር ብሕጊ ኢያ ትረግእ እዚ ፅግርግር ዝመናግስቱ ከም ሕሱም ዝቕጥቅጠና ዘሎ ስርዓት ግን ሕጊ ትባሃል ንኸይትግበር፡ ቅድም ሃገር እሞ ነጻ ነውጽእ ሕግስ ነርክበሉ እናበለ ሒዙና'ዩ ጸኒሑ።
ነቶም ብዛፅባ ሕግን ስርዓትን ዝግደሱ ካኣ እናቐንጸለ ኣብ ድላዩ በጺሑ፡ ንሕና እቶም ደቂ ሕግን ደለይቲ ሕግን ግን ድላይና ኣይረኸብናን፡ ግን ክንሓስበሉ ይግባእ ነዚ ብመገዲ ጉባኤ ክንበጽሖ ንደሊ ዘለና ዝፅንቅፉ ካብቲ ናቱ ድላይ ዝፍለ ድላይ ዘለዎም ኣይኮኑን፡ ሕጋዊ መንግስቲ ዝቃወሙ እቶም ኣልቦ ሕጊ እናነበርና ኣብ ፅግርግር ዘለዎ ሃዋህው ክንነብር ዝደልዩ ክምታ ናቱ ብዘይ ሕጊ ክገዝኡ ዝደልዩ ጥራይ ኢዮም።
ይኹን እምበር እናተሳሓሓብካ ዝጠፍእ እምበር ዝፍታሕ ነገር የለን፡ ንመዋእል ኣብ ሽግር ንነብር ዘለና ኩሉ ጊዜ ስለ ንስሓሓብን ሽግርና ብግቡእ ስለ ዘይንፈትሕን ኢዩ
ነቲ ናይ ኤርትራውያን ሽዑ ዝነበረ ፍልልይ መዝሚዙ ካኣ መዳያየቢ ንናይ እዋናዊ ፅላምኡ ተጠቒሙ ናብቲ ስዒቡ ንህዝቢ ኤርትራን ህዝቢ ኢትዮጵያን ከም ሕሱም ከም ዝዋግኡ ዝገበረ ኩንታት ጥራይ ኢዩ ኣሳጢሑና፡ እዚን ክንዲዝን ዘሕለፈ ህዝቢ ካብ ተሞክሮኡ ተማሂሩ ነዊሕ ዘይጥምት እንተ ኾይኑ ካኣ ይቃለስ ኣለኹ እናበለ ዝኾነ ይኹን ከየዐወተን ኣብቲ ሕማቕ ነገር ሸንኮለል እናበለን ከም'ዚ ናትና ኢዩ ዝነብር፡፡
ኣብ'ቲ እዋን እቲ ኩልና ብሓባር ንናጽነትና ጠጠው እንተንብል ናጽነት ብሕጊ ምተረኽበ ክንደይ ጀጋኑ ብሂወት ምሃለው፡ ህዝብና ካብዚ ዘሎ ሓሳረ መከራ ድሒኑ ምሃለወ፡ ከምቲ ኩልና እንደልዮ ካኣ ነጻን ምፅብልትን ሃገር ምሃለውትና ግን እዚ ኩሉ ክንረክብ ኣይትዓደልናን ጥራይ ዘይኮነ ኣይተጣበብናን እውን፡ ኩሉ መስመሩ እናሳሓተ ዝበላሸወና ዘሎ ካኣ ሳኣን ስምምፅ ዘይምህላውና ጥራይ እዩ፡ ካልእ ኣይኮነን ንሕሰበሉ።
ኣብቲ እዋን እቲ ተሳማሚፅና እንተንኸውን ካኣ ካብ ባፅዳዊ መግዛእቲ ወሪስናዮ ዝነበርና ስልጣኔን ምፅብልናን ዓቂብና ነጻ ህዝቢ ኴና ምሃለና፡ ካብቲ ኩሉ ብሰንኪ ናይቲ ኣብ ብረታዊ ቃልሲ ናይ ሰላሳ ዓመታት ውግእ ዝስዓበ ፅንወትን እዚ ኢዩ ኢልካ ክትቆጽሮ ዘይትኽእል መስዋእትን ድሒንናን፡ ደቅና ኣብ ክንዲ ፋሕ ዝብሉ ይማሃሩ ህዝብና ካኣ ኣብ ክንዲ ዝሳቐ ይሕጎስ ኣብ ክንዲ ዝጠሚ ካኣ ይጸግብ ምሃለወ።
ከምኡ'ውን እዚ ዘሎ ሽቍረራን ራፅድን ተሪፉ፡ ህዝብና ብትብዓት ዝሓርስ ይሓርስ ዝነግድ ይነግድ፡ ልፅሊ ኩሉ ካኣ ብሰላም ይነብር ምሃለወ፡ ግን ኩሉ ሂቡ ስምምፅ ስለ ዝኸልኣና፡ ህዝቢ ኤርትራ ምስ እዚ ኩሉ ፍልጠቱን ምስትውዓሉን ንቐጻሊ ንጥፍኣት ተሳጢሑ ይርከብ ኣሎ፡ እቲ ምስ እዚ ዘሎ ስርዓት ሆ-ኢልካ ምጭዳር ግን ጉድለት ናይ ምሕሳብ ከም ዘለካ ዘመልክትን፡ ካብቲ ኣርሆስ እናተደበቡ ይስሕቁ ዝብሃል ኣባሃህላ ዘይፍለን ስለ ዝኾነ ኩልና ክንሓስበሉን ምስ ህዝብና ክንውግንን ኢዩ ዝግባእ።
ብረታዊ ቃልሲ ከነካይድ ናይ ግዲ ምስ ኮነ ዝተራእየ ጌጋታት እውን ሓደ ካብ ዘገርሙ ኢዩ፡ ብመጀመታ ዝጥቀስ በቲ ንኸተልግሶ ትኽእልዶ ኣይትኽእልን ኣብ ዝብል መስቀላዊ ሕቶ ዝነበረ ገዚፍ ሓይሊ ገዛኢ ህዝቢ ከም ሕሱም እናተሳቐየ ከሎ መን ሓያል ኮይኑ ወጺኡ ሃገር ይቋጻጸር ካብ ዝብል ድልየት ስልጣን ተበጊሶም ህዝቢ ንዘጣፍኡ ደጊፍካ ነቶም ብልቦና ዝልለዩ ኣሕዋትካ ክንዲ ገዚፍ ጸላኢ ከሎ ሓድሕዳዊ ውግእ ኣይጽቡቕን ዝብልን ካልእ ጥዑይን ዘዋጽእን ሕቶ ስለ ዘልዓሉ ምቅዋምን ንኦም ከም ዝጠፍኡ ናይ ምግባር ታሪኽን ኣንጻር ህዝባውን ሃገራውን ረብሓ ምቅላስን ግጉይን ኢዩ ኔሩ፡፡
ነዚ ሕቶታት እዚ ጥሙታት ኮንካን ተሳማሚፅካን ብግቡእ ሳኣን ምምላስ፡ ጊዜ ናጽነት ተናዊሑ፡ ማእለያ ዘይብሉ ህዝብን ንብረትን ጠፊኡ፡ ህዝባዊ ስልጣን ኣብ ኢድ ተበለጽቲ ወዲቑ ሃገር ትሕመስ ኣላ፡ እዚ ካኣ ነቶም ቱኩራት ሃገራውያን ነንሕድሕድና ክንጣፋእ የብልናን ዝብሉ ቀቲልካስ ነቶም ካብ ድልየትካ ወጻኢ ብዝኾነ መንገዲ ነንሓድሕድካ ዘጣፉኡኻ ምኽታል ብዝተገብረ ጌጋ ኢዩ፡ እምበር ብምስትውዓል በቶም ዘስተውፅሉ እናተመራሕካ ቅኑፅ መንገዲ እንተዝትሓዝ ቃልሲ ጥዑይ ውጽኢት ምተረኽቦ፡ ብኡ ካኣ ጠለምቲ ፅድል ኣይምረኸቡን ዝኾነ ይኹን ሽግር ኣብ ልፅሊ ህዝቢ ኤርትራን እዚ ኩሉ ዝርኤ ዘሎ ሃገራዊ ሽግርን ኣይምሃለወን።
ዝኾነ ኮይኑ እዚ ኩሉ ዘጽሕፈኒ ዘሎ፡ ቀንዲ ነቲ ኣብ ኤእዋኑ ብሰንኪ ስምምፅ ዘይምህላውና ነጥፍኦ ዘለና ፅድል ንምብራህ ኢዩ፡ እሞ እቲ በብእዋኑ ብሰንኪ ሓድነት ዘይምህላውና ነጥፍኦ ዘለና ፅድላት ቆጺርካ ዘይውዳእ ስለ ዝኾነ እዚ ዝጠቐስኩዎ ከም መዛኻኸሪ ኢዩ፡ ነቲ ኩሉ ካልእ ኩልና ንፅዘቦ ስለ ዘለና ካኣ እዚ እኹል ኢዩ ባሃላይ ኢየ፡ ንድሕሪ ሕጂ ከምኡ ዝበለ ምትፅንቓፍ ከይንደግም ግን ምጥንቃቕ የድሊ ኣሎ፡ ምኽንያቱ ጌና ሃገርና ኣብ ክንደይ ከታሓሳስብ ዝኽእል ቀራና መገድታት ኢያ ዘላ፡ መከራና ንምውዳእ ብዙሕ ምብልሓትን ዓቢ ህዝብን ሃገርን ንምድሓን ዝሕግዝ ጥበብን ዝድለየሉ እዋን ኢና ዘለና፡ እቲ ኩንታት ሃዋኺ ክነሱ እቲ ቃልሲ ግን ኣይበሰለን።
ጌጋታትና እንርእየሉን ኣብ ዝመጽእ ጠመተ ንእንገብረሉ ኩሉ ዓይነት ፍታሓት ክድህስስ ከም ዘለዎ ከነታባብዖን ብውጽኢቱ ምሉእ ህዝቢ ዝቐስነሉ ኩነታት ከም ዝፍጠር ክግበር ከም ዘለዎ ክንደፋፍእ ዳኣምበር ነቲ ምትፅንቓፍ ከም ልሙድ ክንወስዶ ኣይግባእን፡እዚ
ጉባኤ እዚ ዝተኻፈለ ይካፈሎ ውጽኢቱ ንረብሓን ቅሳነትን መላእ ህዝቢ ኤርትራ ኢዩ ህዝቢ ኤርትራ ሎሚ እንተስ ብሰማይ እንተስ ብምድሪ ረዳኢ ፍጠረልና ኢዩ ጸሎቱ።
ሎሚ ከም ኤርትራውያን ሽግርና ንምፍታሕ ዘየኽእለና ዘሎ ምኽንያት እንታይ ኢዩ እቲ ኣብ ጉፅዞ ቃልሲ ብሰንኪ ዘይምስምማፅና በብእዋኑ ዘጋጥም ዝነበረ ፍልልያትከ ምኽንያቱ እንታይ ኔሩ ዝብሉ ሕቶታት እናልዓልና እንተ ተማራሚርና ሓደ ዘይተፈወሰ መሰረታዊ ሽግር ከም ዘለና ክፍለጥ ይካኣል ኢዩ፡ ሽዑ ነቲ መሰረታዊ ኮይኑ ዝጸንሐን ንዘሎን ሽግር ኣብ ምፍታሕ ዘየሳማማዓና ብኸመይ ከም ንፈትሖ ንጣበብ ማለት ኢዩ።
ማንኛውም ድርጅት ሕጎችና ደንቦች የሚያወጣለትና ኀላፊነትን የሚወስድ አባወራነት ያስፈልገዋል፡፡ የመሪነት ኀላፊ ከሌለ ግን ከፍተኛ መደናገርን ከመፍጠሩም በላይ ሥራውን ከንቱና ፍሬ ቢስ ያደርገዋል፡፡ እንግዲህ በኅብረተ ሰብ መካከል ከሁሉ አነስተኛ የሆነና በእግዚአብሔር የተቀደሰ ቤተ ሰብ አባወራነት ሲኖረው አስገራሚ አይደለም፡፡
በዚህ ረገድ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ በተፈጠሩት በአዳምኛ በሔዋን ቅንጅቱ እንዴት ሊታይ ይችላል? “አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና በኋላም ሔዋን ተፈጠረች” ሲል ሐዋርያው ጳውሎስ ያሳስበናል፡፡ በሥነ ፍጥረት ውስጥ ቀጥተኛ የሆነ የአፈጣጠር ተራ አለ፡፡ አዳምም ከሔዋን የተፈጠረ ሳይሆን ሔዋን ከአዳም የተፈጠረችና ለእርሱም ረዳትና ጓደኛ እንድትሆን እግዚአብሔር አዳምን ወደ ሔዋን ያመጣ ሳይሆን ሔዋንን ወደ አዳም እንዳመጣ እንገነዘባለን፡፡ ይህንም ቀደምትነት አዳም ለእንስሳቱ በሙሉ ስምን በማውጣት ለሔዋንም ስምዋን በመስጠት ገልጦ አሳይቶአል፡፡ በእርሷ ላይ ያለውን አባወራነት ያመለክታል፡፡ በዚህም ሁኔታ ፍጹም ደስታና አንድነት በመካከላቸው ይታይ ነበር፡፡ እንዲሁም ከመጀመሪያ ጀምሮ በባልና ሚስት መካከል ያለው ግንኙነት በአብና በወልድ መካከል ያለውን ውብና ምስጢራዊ ግንኙነት እንዲያመለክት በሐዋርያው ጳውሎስ በሚቀጥለው ቃል ተገልጦልናል፡፡ “የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ፡፡” በተጨማሪም ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በባልና ሚስት መካከል ያለው ግንኙነት በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል እንዳለው የተቀደሰ ዐይነት ግንኙነት መሆኑን ይገልጻል፡፡
በምሳሌና በትእዛዝ መጽሐፍ ቅዱስ ደረጃ በደረጃ የአባወራነት ሕግ ለባል ምን እንደሚል ይገልጽልናል፡፡ እርሱም ለቤተ ሰቡ ጀማሪና አቅኚ በመሆኑ ውሳኔዎቹን ለማውጣት ኀላፊነትና ውሳኔዎቹን ለመፈጸም እግዚአብሔር የሰጠው መንፈሳዊ ሥልጣን እንዳለው እንረዳለን፡፡ ከውድቀትም በኋላ እግዚአብሔር ለሴቲቱ “ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም ገዢሽ ይሆናል” ካለ ጊዜ ጀምሮ አንዳንድ ወንዶች አባወራነት በወንድ በኩል የመጨቈኛ ቃል በማስመሰል ይመለከቱታል፡፡ ዛሬም በአብዛኛው የዓለም ሰዎችና እንዲሁም በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ዘንድ ነገሩን በዚህ መልኩ ያስተውሉታል፡፡ ስለዚህ በቀጥታ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ተመልሰን እግዚአብሔር የሰጠንን ትክክለኛ ምሳሌ መመርመር ይገባናል፡፡ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ራሱን አሳልፎ እስከሚሰጥ ድረስ ፍቅሩን አስረዳ፡፡ እንዲሁም ደግሞ ባል በአባወራነቱ ሲጠቀም ከክርስቶስ ጋር በተመሳሳይ ርኅራኄና ፍቅር ሚስቱን እንዲወድዳት ሐዋርያው ጳውሎስ ያስተምራል፤ “ባሎች ሆይ! ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደደና ራሱን ስለ እርስዋ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፡፡” ይላል፡፡ ሥልጣን ኀላፊነትና ፍቅር በአባወራነት ላይ የሚታዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ከነዚህም ነገሮች ውስጥ አንዱ ቢጐድል ሁሉም ይበላሻሉ፡፡ የዚህም ውጤት በባልና ሚስት መካከል ችግር መፍጠር ነው፡፡
አባወራነት ካለ መታዘዝ ይኖራል፤ አንዱ ለኀላፊነት ከታጨ ሌሎቹ ለእርሱ መታዘዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ ለቤተ ሰብ ከእግዚአብሔር የተሰጠ መለኮታዊ ምሳሌ ሴት የባልዋን አባወራነት እንድትቀበልና ለእርሱም እንድትታዘዝ መሆኑን በሐዋርያ ጳውሎስ ቃል ተግልጦአል፡፡ “ሚስቶች ሆይ ለጌታ ኢየሱስ እንደምትታዘዙ ለባሎቻችሁ ታዘዙ፡፡” ክርስቶስ ለአብ እንደ ታዘዘ፥ ሚስት ለባልዋ ስትታዘዝ የጌታን መንገድ በመከተልዋ ከፍተኛ ጥሪዋን ስታከብር እናያለን፡፡ የእርስዋ ለባልዋ መታዘዝ የሚዘክረው ቤተ ክርስቲያንም በክርስቶስ እንደምትታዘዝ የሚያገለግል ምሳሌ እንደ ሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ ያስረዳናል፤ “ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትታዘዝ እንዲሁም ሚስቶች በሁሉ ነገር ለባሎቻቸው ይታዘዙ” ይላል፡፡
በአሁኑ ወቅት ግን ብዙ ባለትዳር ሴቶች በዓለም አመለካከት በማየት መታዘዝን እንደ ባርነት በመቊጠራቸው ራሳቸውን ዐርነት ያወጡ ስለሚመስላቸው ከመታዘዝ ለማምለጥ ይፈልጋሉ፡፡ ሰይጣን ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ መታዘዝን ባለመታዘዝ ለውጦአል፡፡ ይኸውም በፍቅር ለእርሱ ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ እስከሚሰጥ ድረስ ለሚወድዳት ባል በቅንጅት ውስጥ በመታዘዟ ደስ ሊላት ይገባል፡፡ ነገር ግን ሰይጣን በሴትነቷ እንደ ዕቃና እንደ ገረድ እንድትሆን ለሚቈጥር ወንድ ወደ መገዛትና ወደ ባርነት አልፋ የተሰጠች እንደ ሆነች አድርጎ ስለ ቀየረው ሚስት ለባል መታዘዟ ቅር ይላታል፡፡ ይህም እንደ እግዚአብሔር ዕቅድ አይደለም፡፡ ስለዚህ ዐሳባችን በዙሪያችን በሚሰፍን ግብረ ገብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል በሚሠራ በመንፈስ ቅዱስ እንዲታነጽ ያስፈልጋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚል “አእምሮአችሁ ታድሶ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ የዚህን ዓለም ሰዎች ክፉ ጠባይ አትከተሉ፡፡” ሚስት ለባልዋ መታዘዝ ማለት በቤተ ሰብ መካከል በውይይትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አለመካፈል ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሲመካከሩ እግዚአብሔር የባልዋን ዐሳብና ፍላጎት እንዲያቀና ትማጸናለች፡፡ ሆኖም በብርቱ ነገር የዐሳብ አለመግባባት በመካከላቸው ሲከሠት፥ ባልዋ ውሳኔ እንዲሰጥበት ዝግጁ ሆኖ ውጤቱ የቀና እንዲሆን ለእግዚአብሔር አደራውን ታስረክባለች፡፡
ሣራ ከአብርሃም ጋር ወደ ሰው አገር ስትጓዝ በጣም ውብ ሴት በመሆንዋ አብርሃም ለሕይወቱ ይፈራ ነበርና፥ ሁለት ጊዜ እኅቴ ናት ብሎ ሰዎቹን ሲያታልል በዚህ ለአብርሃም ታዘዘች፡፡ አልታዘዝም አላለችውምና ምንም እንኳ በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ብትገባም፥ የአብርሃምን ትእዛዝ ተቀብላ እግዚአብሔር እንደሚያድናት አመነች፡፡ እርሷ በአብርሃም “ግማሽ ውሸት” (በአባቱ በኩል እኅቱ ነበረችና) ባትስማማ ይሻል ነበር ብለን ብናስብ ዐዲስ ኪዳን ስለዚህ ነገር ምንም አይናገርም፡፡ ሆኖም ሣራ ለባልዋ ስለ መታዘዝዋ እያመሰገንዋት ክርስቲያኖች የሆኑ ሴቶች ሁሉ ምሳሌነትዋን አርኣያነትዋን እንዲከተሉ ያሳስባቸዋል፡፡ “በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋኅና ጭምት መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ፡፡ ... እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት …” ውበቱ ሰዎች ከሚረዱት ይህ ቀረሽ ከማይባለው ውጫዊ የሰውነት ውበቷ እጅግ የላቀ መሆኑን ከዚህ አንቀጽ ልናስተውል እንችላለን፡፡
በአብርሃምና በሣራ መካከል የተለመደው ግንኙነት በአንድ ወቅት ለጊዜው እንደ ተበላሸ መጽሐፍ ቅዱስ ይተርካል፡፡ እግዚአብሔር ልጅ እንደሚወልዱ ተስፋ ሰጥቶአቸው ነበር፤ ሆኖም ሳይወልዱ ለብዙ ዓመታት ቈዩ፡፡ በዚህም ምክንያት በመካከል ሣራ የራሷን ርምጃ ለመውሰድ ፈለገች፡፡ አብርሃምም በአካባቢው የነበሩትን አረማውያን ልማድ ተከትሎ አጋር ከተባለች የሣራ አገልጋይ ልጅ እንዲወልድ ሣራ ባልዋን መከረችው፡፡ እግዚአብሔር ከሰጣት ኀላፊነት በመውጣት ይህን የመሰለ የእምነት ጒድለት በማሳየቷ የባሏ መሪ ለመሆን ሞከረች፡፡ ከዚህም በመቀጠል አብርሃም ከእርሱ ኀላፊነት ወጥቶ ሣራ ባለችው ነገር ተስማማ፡፡ የዚህም ስሕተት ውጤት እስከ ዛሬ ድረስ የሚሳዝን ሆኖ በግልጽ ይታያል፡፡ ምክንያቱም የእስራኤል ትውልድ ከሣራና ከአብርሃም በተገኘው ልጅ በይሥሐቅ በኩል ሲቈጠር፥ የዐረብ ትውልድ ግን ከአብርሃምና ከአጋር በተገኘው በእስማኤል በኩል ሲቈጠር ይታያል፡፡
የአብርሃም ልጅ ይሥሐቅ ሚስቱን ርብቃን ፈልጎ ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ሁለቱን ቢያገናኛቸውም ይሥሐቅ ግን ቤተ ሰቡን በትክክል ለመምራት ችግር ነበረበት፡፡ በዚህም ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሁኔታው እየባሰ ሄዶ በመጨረሻ በአንድ ወቅት አማራጭ በሌለው ሁኔታ ላይ ወደቀ። ይሥሐቅ በሚስቱ አስተሳሰብ ሥር በመሆኑ በታናሽ ልጁ በያዕቆብ ተታለለ፡፡ ይሥሐቅ ቤተ ሰቡን ለመምራት ባለመቻሉና ሚስቱም ለእርሱ ሳትታዘዝ በራስዋ ፈቃድ ለመኖር በመሻትዋ ቤተ ሰቡም በሙሉ ለከፋ ችግር ተጋለጠ፡፡
ሔዋን ብቻዋን ስትሆን ለምን መልካምና ክፉ ወደሚያስታውቀው ዛፍ ቀረበች? ከእግዚአብሔር የተከለከለውን ፍሬ ለመወሰድ ውሳኔ ስታደርግ ምክርን ለመጠየቅ ወደ ባለቤትዋ ለምን አልሄደችም? አንድ ጊዜ ነገሩን በገዛ እጇ ከወሰደች በኋላ አዳም አባወራነቱን ስላልተጠቀመበት በእርሷ በተያዘ መሪነት ተሸነፈ፡፡ ምን ዐይነት አሰቃቂ ውጤት እንዳስከተለ ሁላችን እናውቃለን፡፡
ላገቡት፥ በጋብቻችን ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠውን አርኣያ በአግባብ እንፈጽማለንን? እኔ ባል ስሆን ከእግዚአብሔር የተሰጠኝን አባወራነት እፈጽማለሁን? የቤተ ሰቤ መሪ ሆኜ ኀላፊነቱን እወስዳለሁን? ይህን አባወራነት በእውነተኛ ፍቅር ራሴን መሥዋዕት እስከማደርግ ድረስ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝን? ለምሳሌ ዱሮ ለሌላ ነገር የተጠቀምኩበትን ገንዘብና ሰዓት ልማዶችና ከጋብቻ በፊት የወድድኳቸውን ጓደኞች ለሚስቴ ስል ለመተው ዝግጁ ነኝን? ከዚህ በፊት ያልፈጸምኳቸውን አንዳንድ ነገሮች ለእርሷ ስል እፈጽማለሁን? የሚመቸውን ረዳት-ጓደኛ ለመቀበል አዳም ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ ሔዋንም ሕይወት እንድትቀበል የአዳም ሰውነት ተሰብሮላት ነበር፡፡ ለእንደዚህ ዐይነት መሥዋዕት ዝግጁ ነኝን?
እኔ ሚስት ስሆን ለባለቤቴ በመታዘዜ ለጌታ እየሱስ እንደምታዘዝ እገልጣለሁን? ለባለቤቴ እንደ መታዘዜ የጌታ ኢየሱስን መንገድ እንደምከተል አስተውላለሁን? ከባለቤቴ ጋር በሰላም እንድኖር በቤተ ሰብ ውስጥ የዘመዶቼን ጣልቃ ገብነት ለመቈጣጠር ዝግጁ ነኝን? ስለ ልጆቻችን አስተዳደርና ስለ ገንዘባችን አጠቃቀም የባለቤቴን ውሳኔዎች ለመቀበል ዝግጁ ነኝን? በዕለት ፕሮግራማችን ላይ የእርሱን ምክር መቀበል እችላለሁን? ዋናው ቁም ነገር የሚስትነትና የእናትነት ኀላፊቴን ለመጠበቅ በእምነት የራሴን ፕሮፌሽናል ሥራ ለመተው ዝግጁ ነኝን? እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ሁሉ እንደሚሰጠን አምናለሁን? እግዚአብሔር በእኔ ውስጥ ደስ የሚያሰኘውን ጭምት መንፈስ እንዲፈጥር እለምነዋለሁን?
ወደ ፊት ስለማገባት ሚስት ሳስብና ስጸልይ ምን ብዬ ራሴን መጠየቅ ይገባኛል? ለእርስዋ ኀላፊነትንም እስከምወስድ ድረስ እወዳታለሁን? እርስዋ በደስታ እንድትታዘዝልኝ እንድትከተለኝ እኔ ለእርሷ መልካም መሪ መሆን እችላለሁን? ስለዚህ ባለመታዘዟ እኔን የማታከብር ሴት እውነተኛ ሚስት ትሆናለች ብዬ አላስብም፡፡
ወደ ፊት ስለማገባው ባል ሳስብና ስጸልይ እስከምታዘዝለት ድረስ አከብረዋለሁን? እኔ ለትዳር የምመርጠውን ወንድ እስከምታዘዝለት የማላከብረው ከሆነ ባላገባው ይመረጣል፤ ምክንያቱም ትዳራችን ውሎ ዐድሮ ችግር ላይ ይወድቃልና፡፡
በባልና በሚስት መካከል ያለው የፍቅር ግንኙነት ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አብነት እንዲገልጥና የጋብቻችን አመሠራረትም እንደ እርሱ ፈቃድ እንዲሆን የሕይወት ቃል ለዓለም ሰዎች በማቅረብ ቤተሰቦቻችንም በእነርሱ መካከል ሆነው እንደ ሻማ እንዲያበሩ እግዚአብሔር ይርዳን!
አማርኛ ፡ የኢትዮጵያ ፡ መደበኛ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። ከሴማዊ ፡ ቋንቋዎች ፡ እንደ ፡ ዕብራይስጥ ፡ ወይም ፡ ዓረብኛ ፡ አንዱ ፡ ነው። በአፍሪካ ፡ ውስጥ ፡ ደግሞ ፡ ከምዕራብ ፡ አፍሪካው ፡ ሐውሳና ፡ ከምሥራቅ ፡ አፍሪካው ፡ ስዋሂሊ ፡ ቀጥሎ ፡ 3ኛውን ፡ ቦታ ፡ የያዘ ፡ ነው።[1] እንዲያውም ፡ 85.6 ፡ ሚሊዮን ፡ ያህል ፡ ተናጋሪዎች ፡ እያሉት ፣ አማርኛ ፡ ከአረብኛ ፡ ቀጥሎ ፡ ትልቁ ፡ ሴማዊ ፡ ቋንቋ ፡ ነው። የሚጻፈውም ፡ በአማርኛ ፡ ፊደል ፡ ነው። አማርኛ ፡ ከዓረብኛና ፡ ከዕብራይስጥ ፡ ያለው ፡ መሰረታዊ ፡ ልዩነት ፡ እንደ ፡ ላቲን ፡ ከግራ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ መጻፉ ፡ ነው።
የሐማራ * ግዛት ፡ ተብሎ ፡ የሚታወቀው ፡ ቦታ ፡ በአሁኑ ፡ መካከለኛና ፡ ደቡብ ፡ ወሎ ፡ ይገኝ ፡ እንደነበር ፡ በታሪክ ፡ ይጠቀሳል[2]። ከክርስቶስ ፡ ልደት ፡ በፊት ፡ ከ200 - 130 ዓ.ዓ. ፡ የነበረው ፡ አጋታርከስ ፡ ስለ ፡ ቀይ ፡ ባህር ፡ እና ፡ አካባቢው ፡ ሲጽፍ ፣ ትሮጎዶላይት ፡ ያላቸው ፡ ህዝቦች --τής Kαμάρ λέξιςα ( የካማራ Camàra ቋንቋ) ወየንም ፡ Kαμάρα λέξιςα ( ካማራ Camàra ቋንቋ) ይናገሩ ፡ እንደነበር ፡ ዘግቧል[3]። ከዚህ ተነስተው ፡ የተለያዩ ፡ ታሪክ ፡ አጥኝወች ፡ የአጋታርከስ ፡ ካማራ ፡ ቋንቋ ፡ የአሁኑ ፡ አማርኛ ፡ ወላጅ ፡ እንደሆነ ፡ ያስረዳሉ[4][5][6]።
ትክክለኛው ፡ አማርኛ ፡ አንዳንዴ ፡ «የንጉሥ ፡ ቋንቋ» ፡ ወይም ፡ ደግሞ ፡ «ልሳነ-ንጉሥ» በመሰየም ፡ ታወቋል። አማርኛ ፡ ልሳነ-ንጉሥ ፡ የሆነው ፡ በ1272 ዓ.ም. ከዛጔ ሥርወ መንግሥት ፡ በኋላ ፡ አጼ ፡ ይኩኖ ፡ አምላክ ፡ ሰሎሞናዊውን ፡ ሥርወ-መንግሥት ፡ መልሶ ፡ ሲያቋቁም ፡ ነበር።[1] አማርኛ ፡ ልሳነ-ጽሑፍ ፡ መሆን ፡ የጀመረው ፡ በ14ኛው ፡ ክፍለ ፡ ዘመን ፡ ላይ ፡ ሲሆን ፡ ይህንንም ፡ ያደረገው ፡ ሁሉንም ፡ የግዕዝ ፡ ፈደላትን ፡ በመውሰድና ፡ 6 ፡ አዳዲስ ፡ የላንቃ ፡ ፊደላትን ፡ (ማለትም ሸ ፣ ቸ ፣ ኘ ፣ ዠ ፣ ጀ ፣ ጨ) እና ፡ ኸን ፡ በመጨመር ፡ ነበር።[1] ነገር ፡ ግን ፡ በጽሑፍ ፡ ይበልጥ ፡ መስፋፋት ፡ የጀመረው ፡ ከአጼ ፡ ቴዎድሮስ ፡ ጀምሮ ፡ ሲሆን ፡ ለዚህም ፡ በተለይ ፡ አስተዋጽኦ ፡ ያደረገው ፡ ጸሐፊያቸው ፡ ደብተራ ፡ ዘነብ ፡ ነው።[1] አማርኛ ፡ በተለይ ፡ የተስፋፋው ፡ የዳግማዊ ፡ አጼ ፡ ምኒሊክን ፡ የግዛት ፡ ማስፋፋት ፡ ዘመቻ ፡ ተከትሎና ፡ እንዲሁም ፡ ዘመናዊ ፡ ትምህርት ፡ ኢትዮጵያ ፡ ውስጥ ፡ ከተጀመረ ፡ በኋላ ፡ ነበር።[1]
አማርኛ ለብዙ ዘመናት በእጅ ሲጻፍ ቆይቶ በ፲፱፻ ዓ.ም. ገደማ በማተሚያ መሣሪያ ሊከተብ ችሏል። የግዕዝን ፊደል በዶ/ር ኣበራ ሞላ ፈጠራ ወደ ኮምፕዩተር ገብቶ ከ፲፱፻፹ ዓ.ም. ወዲህ በኮምፕዩተር መጠቀም ከመቻሉም ሌላ በዩኒኮድ ዕውቅና ኣግኝቷል። ይህ የተስፋፋ ገጽም የቀረበው በእዚሁ ሥርዓት ሲሆን በቋንቋው የተጻፉ መረጃዎች ቊጥሮች እያደጉ ነው። የዓማርኛ ፊደልና ቋንቋም ዕውቅና እያደገ ስለመጣ በእጅ ስልኮችም በሚገባ ሥራ ላይ እየዋለ ነው። ኣፕል የቋንቋ ገበታዎቹን ሌሎችም እንዲጠቀሙበት በ፳፻፯ ዓ.ም. ስለከፈተ ዓማርኛን እንደሌሎች የዓለም ባለፊደል ቋንቋዎች መርጦ መጠቀም ተችሏል። በ፳፻፰ ዓ.ም. ግዕዝ የመጀመሪያን የኣሜሪካ የባለቤትነት መታወቂያ (ፓተንት) ኣግኝቷል። [1]
በየካቲት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. አማርኛ ወደ ማናቸውም ሌላ ቋንቋ በኮምፒውተር በቀላሉ ወደሚተረጎሙት ቋንቋዎች ገብታለች። ሆኖም የትርጉሙ ጥራት ከፍ ያለ ሳይሆን ስኅተቶች የተሞላበት ሆኖ ቀርቷል።
28 ቃላት ወይም 13.5% ከግዕዙ በምንም አይለዩም (አንተ፣ እንስሳ፣ ዓሣ፣ ፍሬ፣ ሥጋ፣ ደም፣ ዐይን፣ አፍ፣ እግር፣ ክንፍ፣ ልብ፣ ነከሰ፣ ሞተ፣ ቆመ፣ ዞረ፣ አሠረ፣ ፀሐይ፣ ኮከብ፣ ባሕር፣ ደመና፣ ሰማይ፣ ነፋስ፣ ጢስ፣ እሳት፣ ሌሊት፣ ዓመት፣ ክብ፣ ስም።)
77 ወይም 37% ከግዕዙ ቃላት በቀጥታ የተደረጁ ናቸው (እኔ፣ እኛ፣ እናንተ፣ ማን፣ ምን፣ የት፣ መቼ፣ ሁሉ፣ ብዙ፣ አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፣ አምስት፣ ረጅም፣ ከባድ፣ ትንሽ፣ አጭር፣ ጠባብ፣ ቀጭን፣ ሴት፣ ሰው፣ ልጅ፣ ሚስት፣ አባት፣ ወፍ፣ ቅማል፣ ዘር፣ ቅጠል፣ ሥር፣ ልጥ፣ ሣር፣ አጥንት፣ ስብ፣ እንቁላል፣ ቀንድ፣ ጸጉር፣ ራስ፣ ጥፍር፣ እጅ፣ ጉበት፣ ጠጣ፣ በላ፣ ጠባ፣ ነፋ፣ ተነፈሰ፣ ሳቀ፣ አየ፣ ሰማ፣ አሠበ፣ ፈራ፣ ገደለ፣ ቈረጠ፣ መጣ፣ ወደቀ፣ ያዘ፣ ጨመቀ፣ አጠበ፣ ሳበ፣ ገፋ፣ ጣለ፣ ሰፋ፣ አለ፣ አበጠ፣ ዝናብ፣ ጨው፣ ጉም፣ አመዳይ፣ አመድ፣ ቀይ፣ ሙቅ፣ ሙሉ፣ አዲስ፣ አሮጌ፣ እርጥብ፣ ቅርብ፣ ሩቅ።)
ከግዕዝ ጭምር ከሰው ልጆች ልሳናት የተበደሩ ሌሎች ቃላት እንደ ዘመኑ ይለያያሉ፦ ከግሪክኛ፣ ከአረብኛ፣ ከፖርቱጊዝኛ፣ ከቱርክኛ፣ ከፈረንሳይኛ፣ ከጣልኛና ከእንግሊዝኛ ቃላት የተቀበሉባቸው ዘመኖች ኑረዋል። እንዲሁም አንዳንድ የአማርኛ ቃሎች ከግዕዝ ይልቅ እንደ ኦሮምኛ ወይም እንደ ኩሻዊ ቋንቋዎች ቃላት ይመስላሉ።
ኣነስ እንታይ ምበልኩ : እዚ ስርዓት ዝውክሎ ፍሉይ ሕ-ስብ ካብ ዘይብሉ እቲ ጸግም ካብ ‘ቲ ዝበሃል ዘሎ ዝለዓለ እዩ ::ምናልባት ካብ ዕለታት ሓንቲ መዓልቲ ንትግርኛ ተዛረብቲ ዝውክል ኮይኑ ብምቅራብ ኣብ ሞንጎ ህዝብና ፍልልያት ክፈጥር ፈቲኑ ይኸውን ወረ እቲ ጸዋታ ‘ሲ ዝተሓላለኸ እዩ ዝነበረ: ካብኡ ናባኡ ኣብ ሞንጎ ትግረ ሰምሃርን ትግረ ባርካን ክፈጥሮ ዝፈተኖ ፍልልያት ‘ሲ ነይሩ እንድዩ::
እቲ ኣምላኽ ክብሩ ይስፋሕ :-እዚ ጉጅለ ንቤህራዊ ይኹን ቀቢላዊ ሃይማኖታዊ ይኹን ኣውራጃዊ ፍልልያት ብምግፋሕ ዝገበሮ ሕልኽልኽ ዝበለ ሸርሕታት ደጊም ብሕገ ኣልቦነቱን : ጨካን: ቅጥዒ ኣልቦ ኣሰራርሕኡን ፈሺሉ እዩ :: ሎሚ ብዚ ጉጅለ ዘይተሳቐየ ክፍሊ ሕ- ስብ የለን ወላ ‘ውን ነታ ነብሱ ዘይውክል ሕሱርን ርኹስን መገዲ እዩ ተጓዒዙ ::
እቶም ቀደም ዝተሰነዑ ሕድሕዳዊ ጎነጻት ‘ውን እንተኾነ ኣልሓምዲሊላህ ዝገደፍዎ ወገናዊ ቅርሕንቲ የለን :እቲ ምንታይ ሲ ቀታልን ተቀታልን ክልተ ኣሕዋት ብምንባሮም ስለ’ዚ ሃገርና ኤርትራ ኣብ መጻኢ ኣብ ዘይተደላይ ኩናት ሕድ ሕድ ክትኣቱ እያ ዝብል ጥርጣሬ ክህልወና የብሉን ::
የግዳስ ምስሉይነት ሳዕሪሩ ሓደ ንሓደ ካብ መስመር ብዝሓለፈ መገዲ “ሓደ ኢና” እናበልካ ብድሕሪት ከኣ ምጽላም ምንሻውን : ንቀቢላኻ ወይ ብሄርካ ኣልዒልካ ምር ኣይን ልሙድ እናኾነ ይኸይድ ስለ ዘሎ ፍልልያቱ ኣሚኑ ተኸባቢሩ ዝነብር ክቡር ሕ-ሰብ ኮይኑ ክቀርብ ክንረባረብ ይግበኣና እዩ ይብል :: እዚ ጥራይ ውን ኣይኮነን ዓብላልነት ዕውት ዘይምዃኑ ኣብ ታሪኽ ተማሂርና እና ‘ሞ መሰላት ካለኦት ከይሓለኻ – ርጉጽ ዝኾነ ሰላም ምስፋን ኣይከኣሉን እዩ ‘ሞ ምክብባር ክዓዝዝ ኣትሪርና ክንሰርሓሉ ኣለና ::
ቆፋሪዎቹ (እንግሊዝኛ፦ Diggers /ዲገርዝ/) ከ1641 እስከ 1643 ዓ.ም. ድረስ በእንግሊዝ አገር የቆየ ኅብረተሠባዊ እንቅስቃሴ ነበረ። በ1641 በኦሊቨር ክሮምዌል ዘመን የመሠረተው ሳባኪው ጄራርድ ዊንስታንሊ ሲሆን ደንበኛ ስማቸው «ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» (/ትሩ ሌቨለርዝ/) ይባል ነበር። ሆኖም ከድርጊቶቻቸው የተነሣ «ቆፋሪዎቹ» ተብለው ይታወቁ ጀመር።
«ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» የሚለው ስያሜያቸው የመጣ ከሐዋርያት ሥራ 4፡32 ቃል[1] መሠረት የምጣኔ ሀብታቸው እኩልነት እምነት ስለ ነበራቸው። ቆፋሪዎቹ ርስትን በ«ማስተካከል» የቆየውን ኅብረተሠብ ለማሻሻል ሞከሩ። ዋና ሃሳባቸው በትንንሽ እርሻ ሰፈሮች ላይ በግብርና ሁላቸው እኩል ሆነው ለመኖር ነበር። በዚሁ ዘመን ከተነሡት ከእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ተቃራኒ እንቅስቃሴዎች አንዱ ናቸው።
1641 ዓ.ም. በእንግሊዝ አገር ኅብረተሠባዊ ሁከቶች የበዙበት አመት ነበር። የፓርላማ ወገን በጦር ሜዳ ላይ በሰፊው ድል አድርገው ቢሆንም የተሸነፈው ንጉሥ 1ኛ ቻርልስ ገና ስምምነት አልፈቀድም ነበር። በመጨረሻ ፓርላማና ሠራዊቱ እንደ አታላይ ይሙት በቃ ፈረዱበት።
የንጉሥ ጉባኤ በአዲስ መንግሥት ጉባኤ ወዲያው ተተካ። የፓርላማም ሥልጣን በጠብ ብዛት ስለ ተደከመ ይህ አዲስ ጉባኤ በሠራዊቱ ተገዛ። ብዙ ሰዎች በፖለቲካ ውስጥ ገብተው የአዲስ መንግሥት ለውጥ እንዴት እንደሚሻሻል ያላቸውን ልዩ ልዩ ሃሣቦቻቸውን እያቀረቡ ነበር። የቀደመውን ንጉሥ ልጅ 2ኛ ቻርልስ በዙፋን ላይ ማስቀመጥ የፈለጉ ወገን ሲኖር እንደ ክሮምዌል የነበሩት መሪዎች ደግሞ ባለ ሃብታሞች ብቻ የሚውከሉበት ፓርላማ ፈለጉ። በጆን ሊልቡርን መጻሕፍት ተጽእኖ የወጣ ተቃራኒ ወገን ደግሞ እያንዳንዱ አዋቂ ወንድ ባላቤት እንዲወከል እንጂ በሀብት መሠረት እንዳይሆን ጣሩ። እነኚህ «አስታካካዮቹ» (/ሌቨለርዝ/) ተባሉ። ከዚህ በላይ «አምስተኛው ንጉዛት ሰዎች» የሚባለው ወገን ሃይምኖታዊ መንግሥት (theocracy) ፈለጉ። ከነዚህ ወገኖች መካከል የዊንስታንሊ ቆፋሪዎች ሥርነቀል መፍትሔ አራመዱ።
ጄራርድ ዊንስታንሊና 14 ሌሎች እራሳቸውን ከአስተካካዮቹ ለመለየት ስማቸውን «ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» ብለው አንድ ጽሑፍ አሳተሙ። ሃሳባቸውን ተግባራዊ አድርገው የጋራ መሬት ለማረስ ከጀመሩ በኋላ ሰዎች «ቆፋሪዎች» ይሉዋቸው ነበር። በቆፋሪዎቹ እምነት ተፈጥሮአዊ አኗርኗር አይነተኛ ነበረ። ዊንስታንሊ እንዳለው «ዕውነተኛ ነጻነት ሰው ምግቡንና ደህንነቱን ባገኘበት ይተኛል፣ ያውም በምድሪቱ ጥቅም ነው።»
በቆፋሪዎች አስተሳሰብ፣ ከኖርማኖች ወረራ (1058 ዓ.ም.) አስቀድሞ እንግሊዞች ቀና፣ ጻድቅ፣ እና በእኩልነት የኖረ ነገድ ሆነው ነበር። ኖርማኖች ከወረሩ በኋላ ግን መንግሥቱን በመያዛቸው መኳንንት ሆኑ፣ ኗሪ እንግሊዞች ግን ተራ ሕዝቦች ሆነው በኖርማኖች ሥር («የኖርማኖች ቀንበር») ተጨቆኑ። ዊንስታንሊ እንደ መሰለው የእንግሊዝ ንጉሥና የእንግሊዝ መንግሥት የኖርማኖች ተከታዮች ስለ ሆኑ መጣል ነበረባቸው።
በሚያዝያ 1641 ዓ.ም. ለመንግሥት ጉባኤ በቀረበው ደብዳቤ መሠረት፣ ብዙ ግለሠቦች በቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታ፣ ወይብሪጅ ላይ፣ በኮብሃም፣ ሳሪ ዙሪያ በጋራ መሬት ላይ አትክልትን ይተክሉ ጀመር፣ ይህም የምግብ ዋጋ ካለፈው ጊዜ ይልቅ ከሁሉ ከፍ ባለ ደረጃ ሲደርስ ነበር። የአቶ ሳንደርዝ ደብዳቤ እንዳወራው፣ «ሰው ሁሉ መጥቶ እንዲረዳቸው ሲለምኑ ምግብን፣ መጠትንና ልብስን በምላሽ እንዲያገኙ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።» አጥሮቹን ሁሉ በመፍረስ የዙሪያው ሕዝብ አንድ ላይ እንዲሠሩ ለማድረግ አሰቡ። በ10 ቀን ውስጥ ቁጥራቸው ብዙ ሺህ እንዲሆን አሳመኑ። «ዕቅድ በእጅ እንደ ያዙ የሚል ፍርሃት አለ።» በዚሁም ወር፣ ቆፋሪዎቹ «የእውነተኛ አስተካካዮቹ መርኅ ተራመደ» የሚባል ጽሑፍና አቤቱታ አሳተሙ።
በዙሪያው ባለርስቶች ጥያቄ፣ የአዲስ አራያ ሠራዊት አለቃ ሰር ቶማስ ፌይርፋክስ ከወታደሮች ጋር ደረሰና ዊንስታንሊንና ሌላ ቆፋሪ ዊልያም ኤቨራርድን በጥያቄ መረመራቸው። ኤቨራርድ ብርቱ ችግር እንደ ፈላ ስለ መሰለው ከእንቅስቃሰው ቶሎ ወጣ። ዳሩ ግን በፌይርፋክስ አስተያየት ቆፋሪዎች ጉዳት የሚያምጡ ስላልነበሩ፣ ባለርስቶቹ ጉዳዩን በችሎት እንዲቀጥሉት መከረ።
ዊንስታንሊ በሰፈሩ ላይ ቆየና ቆፋሪዎቹ ስላገኙት እንቅብቃቤ ለመጻፍ ቀጠለ። የርስቱ ጌታ ፍራንሲስ ድረይክ (ይህ የስመ ጥሩ ተጓዥ ፍራንሲስ ድረይክ አልነበረም) ሆን ብሎ በቅጥ ሊያሳድዳቸው ሞከረ። ወንበዶችን በቡድን አሰብስቦ ብዙ ጊዜ ከመደበደባቸው በላይ አንዴ የጋራ ቤታቸውንም አቃጠሉ። በችሎቱ ጉዳይ ቆፋሪዎች ለራሳቸው እንዳይመሰክሩ ተከለከለ። መረኑ የ«ዘላባጆቹ» (/ራንተርዝ/) ወገን አባላት ተብለው ተፈረደባቸው። (እንዲያውም ግን ዊንስታንሊ የዘላባጆች መሪ ላውረንስ ክላርክሶንን መረንንነትን ስለማስተማሩ ወቀሰው) በችሎቱ ጉዳይ ስለ ተሸነፉ፣ መሬቱን ለመልቀቅ እምቢ ካሉ ሠራዊት በእርግጥ ያስወጣቸው ነበር፤ ስለዚህ ለባለርስቶቹ ደስታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታን በነሐሴ 1641 ተዉ።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሳደዱት ቆፋሪዎች መካከል አንዳንድ በትንሽ ርቀት ወደ ሊተል ሂስ ፈለሱ። 4.5 ሄክታር የመሬት ስፋት ልክ ታረሰ፤ ስድስት ቤቶች ታሠሩ፣ የበጋ ሰብል ተመረተ፣ አንዳንድ ጽሑፍ ታተመ። መጀመርያ በርኅራኄ ያያቸው የኮብሃም ርስቱ ጌታ ካህን ጆን ፕላት በኋላ ዋና ጠላታቸው ሆነ። በሥልጣኑ አማካይነት የዙሪያው ሕዝብ እንዳይረዳቸው አሰናከለ፤ እንዲሁም ቆፋሪዎቹም ሆነ ንብረታቸው በግፍ እንዲበደሉ አደረገ። በሚያዝያ 1642 ዓ.ም. ፕላትና ሌሎች ባለርስቶች ከርስታቸው በፍጹም አባረሯቸው።
«እኛ የዌሊንግቦሮ መንደር በኖርሳምቶን ድኃ ኗሪዎች በይርሻንክ በተባለው በዌሊንግቦሮ ኗሪዎች ጋራ ወና ምድር ላይ ለመቆፈር፣ ለማዳበርና እህልን ለመዝራት ፈቅደን የጀመርንበት መሠረቶችና ምክንያቶች አዋጅ...»
ይህ ሠፈር የተጀመረው ከሳሪ ቆፋሪዎች ግንኙነት የተነሣ ይመስላል። በመጋቢት 1642 ከሳሪው ሰፈር የደረሱ 4 ተልእኮዎች በባኪንግሃምሸር ታሠሩ፤ የያዙትም ደብዳቤ በጄራርድ ዊንስታንሊና በሌሎች ቆፋሪዎች ተፈርሞ ሰዎች በየቦታው ለራሳቸው የቆፋሪ ሠፈር ለማቆምና የሳሪን ሰፈር በስንቅ ለመርዳት የሚል ልማኔ ነበር። «ፍጹም በየዕለቱ» የሚባለው ጋዜጣ እንደሚናግረው፣ እነኚህ ተልእኮዎች ከሳሪ ወደ ሚድልሴክስ፣ ህርትፎርድሺር፣ ቤድፎርድሸር፣ ባኪንግሃምሸር፣ ባርክሸር፣ ሃንቲንግደንሸር እና ኖርሳምቶንሸር አውራጃዎች ከተጓዙ በኋላ ታሠሩ።
በሚያዝያ 10 ቀን 1642 ዓ.ም. የመንግሥት ጉባኤ የኖርሳምቶንሸር ዳኛ አቶ ፔንትሎው በሚከተለው ችሎት «በአቅራቢያው ባሉት አስተካካዮች ላይ» ክስ እንዲያካሄድባቸው ታዘዘ። የአይቫ ቆፋሪዎች እንደ መዘገቡት፣ ከዌሊንግቦሮ ቆፋሪዎች 9 በወህኒ ታስረው ምንም ወንጀል በነርሱ ማረጋገጥ ባይቻልም ኖሮ ዳኛው ነጻ እንዳያስወጣቸው እምቢ ብለው ነበር።
ከሳሪና ከኖርሳምቶንሸር ሠፈሮች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌላ ቆፋሪዎች ሰፈር በአይቫ፣ ባኪንግሃምሸር ተገኘ። ይህም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታ በ14 ኪ.ሜ ይርቃል። የአይቫ ቆፋሪዎች አዋጅ እንዳለው፣ ሌሎችም ሠፈሮች ደግሞ በባርኔት፣ ህርትፎርድሸር፣ በኤንፊልድ፣ ሚድልሴክስ፣ በዳንስተብል፣ ቤድፎርድሸር፣ በቦስዎርስ፣ ግሎስተርሸር እና እንዲሁም በኖቲንግሃምሸር ኖሩ። በተጨማሪ የሳሪ ሰፈር ከተሳደደ በኋላ፣ ቆፋሪዎቹ ልጆቻቸውን በአሳዳጊነት መተው እንደ ተገደዱ ይገልጻል።
በመላ እንግሊዝ አገር የቆፋሪ ሰፈሮች በጠቅላላ ከጥቂት መቶ ሰዎች በላይ አልነበሯቸውም። በባለርስቶችና በመንግሥት ጉባኤ ማሳደድ ምክንያት እንቅስቃሴው በ1643 ዓ.ም. ጨረሰ።
^ «ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።» --ግብረ ሐዋርያት 4፡32
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስጥ ሆነን ሁለተኛ ሣምንታችንን ያዝን። ዕድሜ ለአዋጁ ገንዘቤም አፌም ዐረፉ። አሁን አፌን ሰብስቤ በጊዜ ወደቤቴ ከማምራቴ በፊት በየመሸታ ቤቱ እንደጣቃ ስቀደድ አመሽ ነበር። አንዱ ጆሮ ጠቢ ጠልፎ ቢወስደኝና ድራሼን ቢያጠፋው ለምግብ ያላነሱ ለሥራ ያልደረሱ ልጆቼ ወደ በረንዳ መበተናቸው አይቀርም። በሌላም በኩል አዋጁን ቀድሞ በተዘጋው ኢንተርኔት ሰበብ ብዙ ገንዘብ በቴሌ እበላ ነበር፤ አሁን ግልግል ነው። ሣር አልበላም እንጂ፤ በዚያም ላይ “እምቧ!” እያልኩ እንደከብቶቹ አልጮህም እንጂ፤ ዕድሜ ለህወሓት የለዬልኝ የቤትና የዱር እንስሳ ሆኛለሁ - በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ አይሉ ሁለት ዲፕሎማ ይዤ የማልናገር የማልጋገር የወያኔ ጥፍጥፍ ባሪያ ሆኜ መገኘቴ፤ የሰው ልጅ የደረሰበትን ኢትዮጵያዊ የዕድገት ደረጃ ያመለክታል። ግሩም ዕድገት! ግሩም እንከን የለሽ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊ ሩህሩህ መንግሥት!
ይህ አዋጅ በዓለማችን በቅርቡ እንደሚፈነዳ በጉጉት የሚጠበቀውን የሦስኛውን ኒኩሌራዊ የዓለም ጦርነት አስቀድሞ በኢትዮጵያ በለዬለት ባርነት መልክ ያፈነዳ ፈር ቀዳጅ አዋጅ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው። እኔ በበኩሌ ደግሞ አዋጁ የህወሓትን ማይማዊ ዕብሪትና ለህዝብ ያለውን ከፍተኛ ንቀት አጉልቶ ከማሳየቱም በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሚባለው በምዕራባውያን በተለይም በአሜሪካና በአውሮፓ የሚመራው ወያኔን በሁሉም ረገድ ዕቅፍ ድግፍ አድርጎ የያዘው የበላይ ተቆጣጣሪ ለዚህ ቀበጥ ልጁ ምን ያህል እንደሚንሰፈሰፍለትና የፈለገውን ሁሉ እንዲያደርግ የፈቀደለት መሆኑንም አመላካች ነው። ወያኔዎች በዓለም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ይህን መሰል “አዋጅ”፤ ‘ባገር ሰላም’ ማወጃቸው ሊቃወማቸው የሚችል ዓለም አቀፍ አካል እንደሌለ በማመን ነው። ለሁሉም ፍጡራን መብት እንቆረቆራለን ብለው የእንስሳት መብት አስጠባቂ ድርጅት የሚያቋቁሙት ምዕራባውያን፤ እኛ እንዲህ በግልጽ እሥር ቤት ስንታጎር ለኛ ለ“ሰዎች” የሚሆን እርባና ያለው የተቃውሞ ድምፅ ማሰማት አለመቻላቸው የሚገርም ነው። ይህን ዓይነቱን ግልጽ አድልዖና ወደር-የለሽ ፍርደ-ገምድልነት የሚታይበትን ክስተት double standard ይሉታል እነሱ ራሳቸው፤ እጅጉን ይደንቃል።
ለማንኛውም ይህ ዓለምንና እኛን ተጎጂዎቹን ብቻ ሳይሆን የመንግሥተ ሰማይንና የገሀነመ እሳትን ማኅበረሰባት ሳይቀር በሥላቅ የሚያስፈግግ አዋጅ የተሟላ ለማድረግ የሚከተሉትን አንቀጾች መጨመር አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቴ ቀጣዩ ማስተካከያ እንዲጨመርበት በአክብሮት እጠይቃለሁ። ከፀሐይ በታች ከወያኔ በስተቀር አዲስ ነገር የለምና እየተዝናናችሁ እንድታነቡ ልባዊ ግብዣየ ነው። (ዋናው አዋጅ 31 አንቀጾች አሉት።)
የህዝቡን ደኅንነትና ፀጥታ ለመጠበቅ ሲባል ማንኛውም ዜጋ በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ስለምንም ነገር ማሰብ፣ ህልም ማለም፣ መቀባዠር፣ መቃዠትና በዕንቅፍ ልብ ማውራት የተከለከለ ነው።
ሕገ መንግሥታችንን ከመጥፎ የመኪና አነዳድ ለመከላከል ሲባል ማንኛውም አሽከርካሪ መኪና ውስጥ ገብቶ ሲያሽከረክር ወደግራም ሆነ ወደ ቀኝ መታጠፍ፣ ወደቀኝም ሆነ ወደግራ ፍሬቻ ማሣየት፣ በኋላ ማርሽ የኋሊት መሄድ ወይም በፊት ማርሽ ወደፊት መንዳት፣ እስፖኪዮ መመልከት፣ ነዳጅ መቅዳት፣ ዘይት መለወጥ፣ መኪናን ላባጆ ማስገባት፣ ለሰው ሊፍት መስጠት፣ ቤተሰብ መጫን ወዘተ፣ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ሀገርንና ትውልድን ከሽብር ጥቃት ለመከላከል ሲባል፤ ይህ አዋጅ ተግባራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ አራስ ሕጻናትም ጭምር ማንኛውም ለአቅመ ህዝባዊ እምቢተኝነት የደረሰ ዜጋ ፀሐይ መሞቅ፣ አየር መተንፈስ፣ ውኃ መጠጣት፣ መፀዳጃ ቤት መሄድ፣ ሰውነቱን ማከክ፣ ንፍጡን መናፈጥ፣ ምግብ ጠግቦ መብላት፣ ሰላምታ መለዋወጥ፣ የህወሓታውያንን ህንጻና መኪና ማየት፣ ወደነሱም ማፍጠጥ፣ ከሣሎን ወደ ጓዳ ወይም ከመኝታ ቤት ወደ ሣሎን መንቀሳቀስና ከኮማድ ፖስት ኃላፊዎች ፈቃድ ሳያገኙ ከቤተዘመድም ሆነ ከጓደኛ ገንዘብ መበደር ፈጽሞ የተከለከለ ነው። እነዚህን ሲያደርግ የሚገኝ ተሃድሶ ተሰጥቶት ለስድስት ወር ከርቸሌ ይወርዳል።
ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ታማሚን ለመጠየቅ ወይም የሞተን ለመቅበር ሲሰባሰቡ ሕገ መንግሥታቸውንና በመቶ ፐርሰንት የመረጡትን ዴሞክራሲያዊ መንግሥት እንዳያሙ ሲባል በነዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ በተፈጥሮ በሽታም ሆነ በድንገተኛ አደጋ መታመምም ሆነ መሞት የተከለከለ ነው። ነገር ግን የዜጎች መሞት በግድ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ከህወሓቶች በስተቀር ማንኛውም ዜጋ ኣግአዚና የመከላከያ ሠራዊት በሚገኙባቸው አካባቢዎች በቡድንም ይሁን በግል በመቅረብ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ የተፈለገውን ያህል የሞት መጠን መቀበል እንደሚቻል ኮማንድ ፖስቱ በደስታ ይገልጻል። (የጥይት ግን ይከፈላል)
አካባቢን ከኹከት ለመታደግና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ከሚንዱ አሸባሪዎች ለመከላል ሲባል በአዋጁ ጊዜ ውስጥ ማንም ዜጋ በምንም ምክንያት ጮክ ብሎም ይሁን በለኆሳስ መሣቅም ይሁን ማልቀስ፣ “እሰይ!” በማለትም ይሁን ”ውይ!”፣ “ኡፍ!” በሚልም ይሁን “ኣ! ኣ!” የውስጥ ስሜቱን በገሃድና በኅቡዕ መግለጽ የተከለከለ ነው። የቤት አከራዮችም የተከራዮችን ሣቅና ልቅሶ መጠን በመቆጣጠር ከጣራ በላይ የሚስቁትንና ስቅስቅ ብለው የሚያለቅሱትን በመለየት ለሚቀርባቸው የቀበሌ አስተዳደር ጠቁሞ እርምጃ አለማስወሰድ የተከለከለ ነው።
በለጋሽና አበዳሪ ሀገሮች ህዝባዊ የእምቢተኝነት አመፅ ምክንያት መንግሥት ያጋጠመውን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ ሲባል በነዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ሚስት ከባል ወይም ባል ከሚስት ለሚያገኙት ለእያንዳንዱ ፆታዊ እርካታ ብር አንድ መቶ ለመንግሥት ገቢ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ በዚህ ግንኙነታቸው ውስጥ ግን ጽንስ መቋጠር ወይም ማስቋጠር በጥብቅ የተከለከለ ነው፤ ለእርግዝና ቁጥጥሩ ቤተሰብ መምሪያ፣ ጤና ጥበቃና መከላከያ ሚኒስቴር በትብብር እንዲሠሩ በኮማንድ ፖስቱ ታዘዋል - ለትውልድ ማምከኛም በጀት ተይዞላቸዋል። ባገራችን ያለው የመንግሥትና የህዝብ መተማመን ክፉኛ እየቀነሰ በመምጣቱ ሳቢያ፤ ህዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች መንግሥትን እንዳይሸውዱ ሲባል ይህን መሰሉን የግንኙነት መጠን መቆጣጠር የሚያስችል ባልቦላ (ቆጣሪ) ከፈረንሣይና ከጣሊያን በዕርዳታ በማስመጣት በያንዳንዱ ዜጋ ጭን ውስጥ ለመግጠም መንግሥት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኮማንድ ፖስቱ ቁጭትና እልህ በተሞላት ደስታ ይገልጻል። ይህ መመሪያ የማይመለከታቸው ከ10 ዓመት ዕድሜ በታችና ከ110 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ዜጎችን ብቻ ነው። (ስለዚህ የቀድሞውን “ፕሬዝዳንት” አቶ መቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስን አይመለከትም ማለት ነው?)
ሰሜን ሸዋ አካባቢ ግዳጅ ላይ እያለ የተሰዋው ሃምሣ አለቃ ደሳለኝ የተባለ የህወሓት ዕቃ ተሸካሚ አህያ “ስም አስጠሪ ልጅ ሳይተካ ተሰዋ!” ብሎ በዚህ ሰማዕት ላይ ማላገጥ የተከለከለ ነው። እሱን የሚያስከነዳ አንድ ዓይና ጠብደል ስናር አህያ ተክቶ አልፏልና ዘሩ ባለመቋረጡ የመለስ ራዕይ የተመሰገነ ይሁን። (አብረን ይቺን መፈክር እንበል - “የመለስ ራዕይ በአህዮቻችን ግቡን ይመታል!” - “ይመታል!”) …
የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅ ሲባል በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ማንም ዜጋ የፈለገውን መልበስ የተከለከለ ነው - ሞቀኝ በረደኝ ሳይባል መንግሥት በዝርዝር መመሪያዎች በቀጣይ የሚያወጣቸውን የልብስ ዓይነቶችና የአለባበስ ፋሽኖች አለመከተል የተከለከለ ነው። ከዚህ አንጻር ለምሣሌ ቀይ ፓንት ወይም ቢጫ ካናቴራ ወይም አረንጓዴ ኮፍያ ማድረግ መንግሥትን ስለሚያስደነብር በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ሕገ መንግሥታችንን በኃይል ሊንድ ስለሚችል በአዋጁ ጊዜ ውስጥ ዕቁብና ፅዋ ማኅበር መጠጣት፣ በዕድር ቤቶች መሰባሰብ፣ ከሦስት ወር ያለፈው የተረገዘን ጽንስ ጨምሮ ከአንድ ሰው በላይ ከቤት ውጭ መሰብሰብ ወይም ቆሞ መገኘት፣ መጠጥ ቤት መግባት፣ ቤተመጻሕፍት ውስጥ ወይም በሌላ ቦታ የሆቴል ቤትን የምግብ ዝርዝር ጠቋሚ ሜኑ ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት ጽፍሑ/መጽሐፍ ማንበብ … የተከለከለ ነው።
“በደህና እንዳዋልከኝ በደህና አሳድረኝ” ከሚል የግል ጸሎት ውጪ የዘወትር ጸሎትንና ውዳሤ ማርያምን ጨምሮ ማንም ዜጋ ምንም ዓይነት የምህላና የምልጃ ጸሎት በዚህ የአዋጅ ጊዜ ውስጥ ማድረግ የተከለከለ ነው። ሀገር ሰላም ስለሆነች “ሀገረ ኢትዮጵያን ሰላም አድርግልን፤ የቀድሞ አንድነቷን መልስልን” የሚለውን የጠባቦችና የትምክህተኞች ጸሎት ማድረስና በቅዳሤም ይሁን በሌላ ጸሎት ላይ “እግዚኦ መሓረነ …” ብሎ በዜማም ይሁን በዕዝል ማመልጠን ወይ መጸለይ በጥብቅ የተከለከለ ነው - (ዋልሽ! እዚያ የሾምናቸው ልጆቻችን አሣርሽን ያበሉሻል)።
በኢ.ኦ.ቤ/ክርስቲያን የማሣረጊያ ጸሎቶች ውስጥ የጠቅላይ ሚንስትራችንን የአቶ መለስ ዜናዊንና የዶክተር አባ ጳውሎስን ስም ከብፁዕ አባታችን ከአቡነ ማትያስ ስም ጋር አለማንሣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
የህዳሴያችንንና የሕገ መንግሥታችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ማንኛውም ዜጋ ኢቢሲን ጨምሮ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሚዲያዎች መመልከት፣ ማዳመጥና ማንበብ አለበት፤ ከዚህ በተያያዘ ቢቢሲንና ቪኦኤን ጨምሮ ምንም ዓይነት የውጭ ማስሚዲያ መከታተል በጥብቅ የተከለከለ ነው።
በእንቢልታ ጋዜጣ ቅጽ 1 ቁጥር 49 እትም ”የፖለቲካ ውዝግቡና የሽማግሌዎች ሚና” በሚል ርዕስ የቀረበውን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ጹሑፉ በጣም ጥሩና ሊነበብ የሚገባው ሲሆን፣ በውስጡ ቢካተት የበለጠ ጥሩ ይኾን ነበር ያልኩትን፤ ይችን ጽሑፌን ለአንባቢ እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ።