Proverb
stringlengths 4
244
|
|---|
ለልጅ ጥርስህን፤ ለዝንብ ቁስልህን (አታሳይ)።
|
ለመሀን እምዬ፤ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው። (ለአገልጋይ ~ ለባሪያ) ለመኼድና ለመላወስ፥ አዚዥ ራስ።
|
ለመማር ክፍል መግባት፤ ለመኮረጅ ካሮት መብላት። (ለመኮረጅ ~ ለማለፍ) ለመስማት የፈጠንህ፤ ለመናገር የገየህ ዅን።
|
ለመሪህ አሣ ምሰል።
|
ለመራመድ ያቃታት እግር፥ ለእርግጫ ተነሣች።
|
ለመስማት የፈጠንህ፤ ለመናገርና ለቁጣ የገየህ ኹን። ለመሥራት የሚያፍር፥ መብላት አይደፍር(ም)። ለመሥራት ያፈረ፤ ለመብላት ደፈረ።
|
ለመስጠት አለመቸኮል፥ ከሰጡም ወዱያ አለመጸጸት። ለመስጠት አትቸኩል፤ ሰጥተህም አትጸጸት።
|
ለመብላት የጠፋ ቅቤ፥ ስሞት በአፍንጫዬ ይፈስሳል አለ ድሮ። (ይፈስሳል~ይፈሳል)
|
ለመታማት መፍራት።
|
ለመነኰሴ፥ መልካም ለሴ። (:_ ሙቀት ያለው ጢቢኛ፥ ለከት፥ ሙልሙል) ለመነኰሴ፥ መልካም ልላ።
|
ለመከራ የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው።
|
ለመከራ ያለው መነኰሴ፥ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዚል። ለመጪው ትውልድ፥ አይለጉት ሀኬት።
|
ለመሆኑ ሳይሆን፥ እንዳት ይሆናል? ቢሆን። (ለመሆኑ ~ ለመሆን)
|
ለሙት የለው መብት።
|
ለሚመለከት ለሚያየው፥ ሞት ቅርብ ነው። ለሚስት ያጎርሧል፤ ለተመታ ይክሷል። ለማረም፥ ማን ብልት? ሲሠራው ግን፥ ግድፈት። ለማን ይፈርደ? ለወደደ አይደለም ለወለደ።
|
ለማን ይፈርደ? ለወደደ፥ አይደለም ለወደደ፥ ለወለደ።
|
ለማን ይፈርደ? አይደለም ለወደደ ለወለደ። ለማኝ ቢያብድ፥ ስልቻውን አይጥልም። ለማኝ አያማርጥም፤ ማር አይኮመጥጥም። ለማዕበል ወደብ፤ ለነፋስ ገደብ የለውም። ለማየት የፈለገ፥ አይኑን ይገልጣል። ለማያቅህ ታጠን ብልሀል ሀሰን። ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ።
|
ለማያውቅ ፎገራ ደሩ ነው። ለማያውቅሽ ታጠኝ። ለማይሞት መድኀኒት አለው።
|
ለማይሥቅ ውሻ ነጭ ጥርስ፤ ለማይገላምጥ ድሮ ቀይ አይን ይሰጠዋል። ለማይችለው አይሰጥ።
|
ለማይሰጥ ሰው፥ ሲቸግረው ስጡኝን ማን አስተማረው? ለማይሰጥ ሰው፥ ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው? ለማይሰጥ ሰው፥ ስጡኝን ማን አስተማረው።
|
ለምላጭ የሰጡት ገላ አያምም።
|
ለምሽት መብራት፤ ለመከራ ጊዛ ብልኀት። ለምሽት መብራት፤ ለሥራ ብልኀት።
|
ለምን ላለው፥ ፈጣሪ አለው፤ ጠጅ ለላለው፥ ውሃ አለው። ለምን ሰርግ ይኼዳል? ሰርግ አለ፥ በቤቱ።
|
ለምን ተክዤ? አምላክን ይዤ።
|
ለምን ያለው ስልቻውን፤ ጫን ያለው ኮርቻውን። (ያለው ~ ላለው) ለምን ያለው ስልቻውን፤ ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም።
|
ለምን ጊዛው ነቀዝሽ።
|
ለምኖ ለማኝ፥ ቆቤን ቀማኝ። ለምክንያት ምክንያት አለው። ለምክንያት ድመት ሞተች።
|
ለሞተ አህያ ሰርድ ቢሰጡት፤ ምን ይጠቅማል? ለሞት የለውም መድኀኒት።
|
ለሞኝ ንገረው፥ ምን ይሰማ ብዬ? ለብልኅ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ? ለሞኝ፥ እሳትና ውሃ ቀለብ አይመስለውም።
|
ለሞኝ ከሣቁለት፤ ለቅን ከሮጡለት። (ለቅን ~ ለውሻ) ለሞኝ ጉድድ አያሳዩትም፥ ቤት ነው፥ ብል ይገባበታል። ለሞፈር ቆራጭ፥ ዕርፍ አይታየውም በግላጭ።
|
ለሞኝ፥ ሠኔ በጋው፥ መስከረም ክረምቱ።
|
ለሥልጣን ቢመነኰስ፥ ተያ ሲደንስ።
|
ለሥሡ ፍትፍት አሳይቶ፥ እበት ማጉረሡ። (ማጉረሡ ~ ያጎርሧል) ለሥራ አልደረሱ፤ ከመብሉ አልታገሡ።
|
ለሥራ ወንድ፤ ለሴት ሆድ።
|
ለረጅም መንገድ አትሩጥበት፤ ለረጅም ነገር አትቸኩልበት። ለረጅም ሰው፥ ልብ እና ልብስ ያጥረዋል።
|
ለራሱ ሲቆርስ አያሳንስ። (አያሳንስ ~ አያሳንሱ) ለራሱ አብድ ይሮጣል፥ አትርሳኝ ብል ተከትልታል። ለራሱ አያውቅ ነዳይ፥ ቅቤ ለመነ ለአዋይ።
|
ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ፥ መድኀኒቱ ለአዋይ።
|
ለራሱ የማይረባ፥ ለላላም አይረባ። (ለላላም ~ ለሰውም) ለራሱ ጥላ፤ ለእግሩ ከለላ።
|
ለራስ ምታት ጩህበት፤ ለሆድ ቁርጠት ብላበት። ለራስ ሲቆርሱ፥ አያሳንሱ።
|
ለራስ ቢያወሩ፥ ለቅንቅን (ይሩ)። ለራስ ከበጁ፥ አይታጡ ደጁ።
|
ለራስ ያሉት ማር፤ ለባዕድ ያሉት ሽንኩርት።
|
ለራስ ያሉት ገንፎ አይቀጥን፥ ለላላ ያሉት ገንፎ አይወፍርም። ለራበው ሰው ቆል፤ ለቁልቁለት በቅል።
|
ለራበው ባድ መሶብ ማቅረብ። ለራት የማይተርፍ ዳረጎት። ለርስት ሴቶች ስን ይሞቱበታል። ለሮጠ አይደለም፥ ለቀደመ እንጂ። ለሸማኔ ማገጃ፤ ስለት ማረጃ።
|
ለሰለባ የመጣ፥ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ(ም)። ለሰማይ ምሰሶ፤ የለው ለባዕድ ሥር የለው። ለሰበበኛ ቂጥ፥ መረቅ አታብዚበት።
|
ለሰባቂ ጆሮ(ህን) አትስጠው።
|
ለሰው ልጅ ሲያበሉ፥ ለውሻ ልጅ ያብሉ። (ሲያበሉ ~ ሳያበሉ) ለሰው ልጅ ከሚያበሉ፥ ለውሻ ልጅ ያብሉ።
|
ለሰው ልጅ ከማብላት፥ ለውሻ ልጅ ማብላት። ለሰው ሞት አነሰው።
|
ለሰው ልጅ ዕውቀት፤ ለጦጣ ብልጠት።
|
ለሰው ሞት አነሰው፥ ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ። ለሰው ሰው ነው፥ ልብሱ።
|
ለሰው ቢነግሩት ለሰው።
|
ለሰው ቢናገሩ፥ መልሶ ለሰው፥ ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው። ለሰው ብል መሞት አምላክነት ያሻል።
|
ለሰው ብል ሲያማ፥ ለእኔ ብለህ ስማ።
|
ለሰው ብትል ትጠፋለህ፤ ለእግዛር ብትል ትለማለህ። ለሰው እንግዳ፤ ለአገሩ ባዳ።
|
ለሰው ከበሬታው ሰው፤ ለወጥ ማጣፈጫው ጨው። ለሰው የማይል ሰው፥ ሞት(ም) ሲያንሰው።
|
ለሰው ያስታውቅ፤ ለራሱ አያውቅ። ለሰው ጠላቱ፤ ይወጣል ከቤቱ። ለሰይጣን፥ አትስጠው ሥልጣን። ለሰይጣን እንን ወዳጅ አለው።
|
ለሰጭም አያንሰው፤ ለበዪም አይደርሰው።
|
ለሴት ልጅ እስከ አርባ ቀን ሞቷን፥ ከዙያ ወዱያ ሀብቷን።
|
ለሴት ምሥጢር መንገር፤ በወንፊት ውሃ መቅዳት። (መንገር ~ ማውራት) ለሴት ምክር አይገባትም።
|
ለሴት ምክር አይገባትም፥ መከራ አያስተምራትም። ለሴት ብርቱ፤ ወንድ መድኀኒቱ።
|
ለሴት ደላ፤ ለአህያ ዳውላ።
|
ለሴት ጠላ፤ ለፈረስ ቆላ (አይረባውም)። ለሴትና ለአህያ፥ አይነፍጉም ደላ። ለሴትና ለጉም አይነጉም።
|
ለስሟ መጠሪያ፥ ቁና ሰፋች። (መጠሪያ ~ መጥሪያ)
|
ለሹመት ካልመከሩለት፤ ለጥርስ ካልነከሩለት። (ካልነከሩለት ~ ካልከደኑለት) ለሹመት ያደለው፥ የለማኝ አለቃ ይሆናል።
|
ለሺ ወፍ፥ አንድ ጉሉንጉፍ። ለሺ ፍልጥ፥ ማሰሪያው ልጥ።
|
ለሽማግላ የሚያስተምር በውሃ ላይ ይጽፋል፥ ለሕፃን የሚያስተምር በድንጋይ ላይ ይጽፋል።
|
ለቀለብላባ አማት፥ ሢሶ በትር አላት።
|
ለቀላል (ሰው) ምሥጢር፤ መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር። ለቀማኛ የለውም እጅ፤ ለበቅል የለውም ልጅ።
|
ለቀበጠች አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ለቀባሪው አረዳት።
|
ለቀን ቀጠሮ፤ ለሴት ወይዘሮ።
|
ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው፥ ቀንደ ይከለክለዋል። (ይከለክለዋል ~ ይከልክለው)
|
ለቀጣፊ ይደልዎ ጥፊ፤ ለቀልቃላ ይደልዎ ደላ፤ ለመናጢ ይደልዎ ቡጢ። ለቁንጫ፥ ለምድ ያወጣል።
|
ለቀጣፊ፥ ሬት ሸንኮሩ ነው። ለቀጣፊ ሬት አይመረው። ለቀጣፊ አደራ ስጠው።
|
ለቁንጫ መላላጫ።
|
ለቂጡ ጨርቅ የለው፥ ቆንጆ ያባብላል። ለቅልብልብ አማት፥ ሢሶ በትር አላት። ለቅሶ ሳለ ከቤት፥ ለቅሶ ይኼዳል ጎረቤት። ለቅሶ ሳለ ከቤት፥ ይኼዳል ጎረቤት። ለቅናት፥ የለውም ጥናት።
|
ለቅን እግር አንሥተውለት፤ ለውሻ ሮጠውለት። (ሮጠውለት ~ ሸሽተውለት) ለቆመ፥ ሰማይ ቅርቡ ነው።
|
ለቅን እግር አንሥተውለት።
|
ለቆማጣ፥ አንድ ጣት ብርቁ ናት። ለበራ ወለባ፤ ለውሻ ገለባ።
|
ለበሬ መንጃ፤ ለማሩ መውጊያ፤ ለሸማው መከንጃ። ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ።
|
ለበግ ደጋ፤ ለምቾት አልጋ።
|
ለቡናሽ ቁርስ የለሽ፤ ለነገርሽ ለዚ የለሽ። ለባለጋራህ፥ ብልኅ ኹንበት።
|
ለባለጌ፥ ገድሉ ውርደቱ።
|
ለባዕድ የሰጡት ኮሶ፥ ይወጣል ደም ጎርሦ። ለቤቱ ነጭ ሽንኩርት፤ ለውጭ ግን ቀይ ሽንኩርት። ለቤት ሳማ፤ ለውጭ ቄጤማ። (ቀጤማ ~ ቄጤማ) ለቤት ሳንቃ፤ ለነገር ጠበቃ።
|
ለቤት ሳንቃ፤ ለሰው አለቃ፤ ለነገር ጠበቃ ያስፈልገዋል። ለቤት ባላ፤ ለችግር ነጠላ (ያስፈልገዋል)።
|
ለቤት ሳንቃ፤ ለሰው አለቃ።
|
ለብልኅ ንገረው ምን ይስተው ብዬ፤ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ። ለብልኅ አይነግሩ፤ ለድመት አያበሩ።
|
ለብልኅ አይነግሩ፥ ካልጠየቀ በስተቀር።
|
ለብልኅ አይነግሩ(ም)፤ ለንጉሥ አይመክሩ(ም)። ለብቻው የሮጠ፥ የሚቀድመው የለም።
|
ለብልኅ አይነግሩ(ም)፤ ለአንበሳ አይመትሩ(ም)።
|
ለብዙ ጸልት ማሰሪያው አቡነ በሰማያት። ለቦና ጥጃ ውስ አያንሰውም።
|
ለተማሪ ቆል፤ ለወታደር በቅል። ለተሟጋች መኛ፤ የዳኛ ትእግስተኛ። ለተረታው ያበደረ፥ እሳት ጨመረ። ለተራበ ቂጣ፤ ለተጠማ ዋንጫ። ለተራበ በርገር፤ ላፈቀረ ጠበል።
|
ለተራበ በግብር፤ ለተበደለ በነገር (ተገኘ)። ለተራበ ግብር፤ ለተበደለ ነገር።
|
ለተሸሸገ ምግብ፥ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም።
|
ለተሾመ ይመሰክሩለታል፤ ለተሻረ ይመሰክሩበታል። (ይመሰክሩለታል ~ ይሟገቱለታል)
|
ለተሾመው ይመሰክሩለታል፤ ለተሻረው ይመሰክሩበታል። ለተቀማጭ፥ ሰማይ ቅርቡ ነው።
|
ለተባባሰው፥ ማጭድ አታውሰው። ለተቸገረ የማያዝን፥ ዕንብርት የለውም።
|
ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ፤ ለቅን ይፈርዳሉ።
|
ለትኋን ልም ማጉረሥ፤ ለአፈኛ ሰው መመለስ (አይቻልም)። ለቸኮለ ሰው፥ ዋንጫ አስጨብጠው።
|
ለቸኮለ፥ ዋንጫ አስጨብጠው።
|
ለችግር የጣፈው፥ ቢነግድ አይተርፈው። (የጣፈው ~ የፈጠረው) ለነገ የማይልን ሰው፥ ጅብ በላው።
|
ለኀምሳ ጋን፥ አንድ አልል (ይበቃል)። ለሀብት አባት እንጂ፥ አጎት የለውም።
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.